ኢትዮጵያን ጨምሮ የምስራቅ አፍሪካ ሀገራት 3 ችግሮች በጋራ ከፊታቸው ተጋርጧል ተባለ

ኢትዮጵያን ጨምሮ የምስራቅ አፍሪካ ሀገራት 3 ችግሮች በጋራ ከፊታቸው ተጋርጧል ተባለ

ኢትዮጵያ ነገ ዜና || በዓለም በርካታ ሀገራት ላይ በመሥራት የሚታወቀው ሴቭ ዘ ችልድረን፤ በአፍሪካ ቀንድ ታይተው የማይታወቁ ሦስት ችግሮች በአንድ ላይ ከፊት ለፊት ተደቅኗል ሲል አስታወቀ።

የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ፣ የአንበጣ መንጋ ወረርሽኝ እና የጎርፍ መጥለቅለቅ የአፍሪካ ቀንድን በአንዴ  በተግባር እየፈተኑ የሚገኙ ሦስት ችግሮች መሆናቸውን ግብረ ሰናይ ድርጅቱ ገልጿል።

በድርጅቱ  መግለጫ መሠረት እድሜያቸው ከአምስት ዓመት በታች የሆነ ፣ ከአምስት ሚሊየን ሕፃናት በላይ በከፍተኛ የምግብ እጥረት ተጎድተዋል:: በተጨማሪም የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ደግሞ የአገራቱን ምጣኔ ሀብት እና የጤና ሥርዓት እየጎዳው ይገኛል ነው የተባለው።

በምሥራቅ አፍሪካ በቅርቡ የጣለው ተከታታይ ዝናብ የጎርፍ አደጋ ማስከተሉ አስከትሏል:: የአንበጣ መንጋ ወረርሽኝም በመጪው ሰኔ ወር ተስፋፍቶ ቀጠናውን በከፍተኛ ሁኔታ ሊያጠቃ እንደሚችል ቅድመ ግምት ተቀምጧል።

በመሆኑም ሴቭ ዘ ችልድረን፣ የዓለም ዐቀፍ ድርጅቶች ሁኔታው ከቁጥጥር ውጪ ሊወጣ ይችላል በማለት ሶማሊያን፣ ኬንያን፣ ኢትዮጵያን ችግሩን መቋቋም እንዲችሉ አስቸኳይ ድጋፍ እንዲያደርጉ ተማፅኗል። በእነዚህ አገራት ወረርሽኙ ሚሊየኖች በሚገኙበት የተፈናቃዮች መጠለያ ጣብያዎች ሊስፋፋ እንደሚችልም ድርጅቱ አስታውቋል።

LEAVE A REPLY