በምስራቅ ወለጋ ሰዎች በጅምላ እየታሰሩ መሆኑን ነዋሪዎችና ኦፌኮ ገለፁ

በምስራቅ ወለጋ ሰዎች በጅምላ እየታሰሩ መሆኑን ነዋሪዎችና ኦፌኮ ገለፁ

ኢትዮጵያ ነገ ዜና || በምስራቅ ወለጋ ነቀምቴ ከተማ እና ቡኖ በደሌ በተባሉት ሥፍራዎች ሰዎች በጅምላ እየታሰሩ ነዉ ተባለ።  ይህንን ያሉት የዞኑ ኦሮሞ ፌደራሊስ ኮንግረስ (ኦፌኮ) ቢሮ እና የአካባቢው ነዋሪዎች ናቸው፡፡

የኦሮሚያ ክልል ኮሙኒኬሽን ደግሞ በየትኛውም የክልል አካባቢዎች በወንጀል ሳይጠረጠር በፖሊስ የሚያዝ አካል የለም፤ ሕግ ከማስከበር ዉጭ የማሰር ፍላጎት የለንም የሚል ምላሽ ሰጥቷል፡፡

የምስራቅ ወለጋ የኦሮሞ ፌደራሲት ኮንገረስ ጽ/ቤት ተወካይ አቶ ፈቃዱ አያና ለዶቼ ቬሌ “የኮሮና ቫይረስንለመከላከል እና ለመቆጣጠር አስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ከታወጀ ጊዜ አንስቶ፤ በዞኑ የተለያዩ ስፍራዎችና ከዞኑ ውጭ በቡኖ በደሌ ዞንም በርካታ ሰዎች በመንግስት ጸጥታ ኃይሎች እየታሰሩ ነው፡፡ ከሁለት ቀን በፊትም በቀነምት ከተማ መምህራንን ጨምሮ አስራ ሰባት የሚደርሱ ሰዎች በከተማው ውስጥ በሚገኘው የዞኑ ጤና ቢሮ ቅጥር ግቢ ውስጥ ታስረው ይገኛሉ”  ብለዋል፡፡

በነቀምት ከተማ በሚገኘው የወለጋ ዩኒቨርሲቲ 3 መምህራንም በመንግስት ፀጥታ ኃይሎች መደብደባቸውን  የተናገሩቴ የኦፌኮ አመራር፤ መንግስት የኮሮና ቫይረስ ስርጭትን ለመከላከል ከዚህ ቀደም ታራሚዎችን በይቅርታ እንዲፈቱ ማድረጉን አስታውሰው፣ በከተማው አሁንም በርካታ ሰዎች ያለ ምንም ወንጀል  ወደ ማረሚያ ቤት እየገቡ በመሆናቸው መንግስት ተገቢውን ማስተከያከያ ማድረግ ይጠበቅበታል ሲሉ አሳስበዋል፡፡

በነቀምት ከተማ ነዋሪ መሆናቸውን የገለጹ አስተያየት ሰጪ በበኩላቸው፤ በየመንዱ በተለይም ማታ 12፡00 ሰዓት በኋላ  ወጣቶችን በመያዝ እንደሚደበድቡ፣ ለእስርም ቤቶችም እንደሚዳረጉ ተናግረዋል፡፡ ሰላዊማዊ የሆነዉ ህዝብ በየቤቱ ጭምር እየገቡ እንደሚፈተሹ፣ እንደሚያስፈራሩ እና ሰው ደብቃቹኋል በማለትም ጉዳት በፀጥታ ኃይሎች እየደደረሰ እንደሚገኝ አጋልጠዋል፡፡

የኦሮሚያ ክልል ኮሙኒኬሽን ጉዳዩች ጽ/ቤት ሓላፊ አቶ ጌታቸው  በጉዳዮ ላይ ምላሽ ሲሰጡ፤ “በየትኛውም የክልል አካባቢዎች በወንጀል ሳይተረጠር በፖሊስ የሚያዝ አካል የለም፡፡ የአካባቢውን ሰላም እና ፀጥጣ የሚያደፈርሱ አካላት ካሉ ወደ ፊትም የክልሉ መንግስት የህግ የበላይነትን የማስከበር ሥራ ያከናውናል፡፡ እስካሁን ግን ከህግ ውጭ ወይም ያለምንም ጥፋት ታሰርኩ ያለም ሆነ በደል ደርሶብኛል ብሎ ለእኛ ያመለከተ አካል  የለም” ሲሉ ተደምጠዋል::

LEAVE A REPLY