የተነካኩ 2516 ሰዎች ተለይተዋል፤ ሁለት ወጣቶች ዛሬ የኮቪድ 19 ቫይረስ ተገኘባቸዋል

የተነካኩ 2516 ሰዎች ተለይተዋል፤ ሁለት ወጣቶች ዛሬ የኮቪድ 19 ቫይረስ ተገኘባቸዋል

ኢትዮጵያ ነገ ዜና || ማቆሚያ ባጣው የኮሮና ቫይረስ ሥርጭት ዛሬም በኢትዮጵያ ሁለት ወጣቶች የኮቪድ 19 ቫይረስ ተገኝቶባቸዋል:: የጤና ጥበቃ ሚኒስትሯ ሊያ ታደሰ በዕለታዊ የኮሮና ቫይረስ መግለጫቸው፣ ባለፉት 24 ሰዐታት በተደረገው ምርመራ ሁለት ኢትዮጵያዊያን በቫይረሱ መያዛቸውን አረጋግጠዋል።

በተጠቀሱት ሰዐታት ውስጥ የላብራቶሪ ምርመራ የተደረገላቸው ሰዎች ቁጥር ዘጠኝ መቶ ዐሥራ ሁለት መሆኑን ለማወቅ ተችሏል። ከእነዚህ በርካታ ሰዎች መካከል ሁለት የ20 እና 25 ዓመት ወንድ ኢትዮጵያዊያን ወጣቶች በኮቪድ-19 መያዛቸው ታውቋል።

በኢትዮጵያ በአጠቃላይ በኮሮና ቫይረስ የተያዙ ሰዎች ቁጥር 133 የደረሰ ሲሆን 66 ሰዎች ከቫይረሱ አገግመው፣ ሦስት ሰዎች ደግሞ መሞታቸው ይታወሳል።

ኢትዮጵያ እስካሁን ድረስ ለ18 ሺኅ 754 ሰዎች ምርመራ አድርጋ፣ በዚህ ወቅት 62 ሰዎች በለይቶ ማቆያ ውስጥ ሆነው ሕክምናቸውን እየተከታተሉ ይገኛሉ።

ይህ በእንዲህ እንዳለ ከኮሮና ህሙማን ጋር ቀጥተኛ ግንኙነት እንዳላቸው የታመኑ 2516 ሰዎች ወደ ለይቶ መቆያ ተወስደው ክትትል እየተደረገላቸው መሆኑን የኢትዮጵያ ጤና አገልግሎት አስታውቋል።

ሚኒስትር መሳሪያ ቤቱ ከመጋቢት 3 ቀን 2012 ጀምሮ ከኮቪድ 19 ህመምተኞች ጋር የቅርብ ግንኙነት የነበራቸው ናቸው ካላቸው 2516 ሰዎች 1953 ክትትላቸውን አጠናቀው ወደ ማህበረሰቡ ተቀላቅለዋል። 521 ደግሞ ክትትል እየተደረገላቸው መሆኑ ታውቋል።

እስከሁን በበሽታው ከተጠቁ ህሙማን ውስጥ  43% የሚሆኑት የቅርብ ንክኪ የነበራቸው መሆኑ ተመልክቷል።

LEAVE A REPLY