የአርማታ ብረትን ጨምሮ ከ2.500 ሜትሪክ ቶን በላይ ምርቶች ወደ ሀገር እንዳይገቡ ታገዱ

የአርማታ ብረትን ጨምሮ ከ2.500 ሜትሪክ ቶን በላይ ምርቶች ወደ ሀገር እንዳይገቡ ታገዱ

ኢትዮጵያ ነገ ዜና || የአርማታ ብረትን ጨምሮ የጥራት ደረጃን አላሟሉም የተባሉ ከ2. 500 ሜትሪክ ቶን በላይ ምርቶች ወደ ሀገር እንዳይገቡ መታገዳቸው ተሰማ፡፡

ባለፉት 9 ወራት በተካሄደ የጥራት ቁጥጥር ከውጭ ሀገር ተገዝተው የመጡና ደረጃውን ያላሟሉ፤ ከ2 500 ሜትሪክ ቶን በላይ ምርቶች ወደ ኢትዮጵያ እንዳይገቡ መደረጉን የንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ይፋ አድርጓል፡፡

እንዲታገዱ ከተደረጉት የገቢ ምርቶች መካከል 2 304.94 ሜትሪክ ቶን ጥቅል ብረት ፣ 28.7 ሜትሪክ ቶን የቤት ክዳን ቆርቆሮ፣ 180 ካርቶን ሳሙና እንዲሁም 150 ካርቶን የኤሌክትሪክ ገመድ ይገኙበታል ነው የተባለው፡፡

በተጨማሪም 272 ጥቅል የአርማታ ብረት፣ 19 .770 ጀሪካን ፓልም ዘይት፣ የታሸጉ ምግቦች እና ሌሎችም የገቢ ምርቶች ከጥራት መስፈርት በታች ሆነው ስለተገኙ ወደ ሀገር እንዳይገቡ እንደተደረጉ ከሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ መግለጫ መረዳት ተችሏል፡፡

LEAVE A REPLY