የኮሮና ቫይረስን ለመከላከል የሚያገለግሉ መሣሪያዎች ዳግም እየተከለሰ ነው ተባለ

የኮሮና ቫይረስን ለመከላከል የሚያገለግሉ መሣሪያዎች ዳግም እየተከለሰ ነው ተባለ

ኢትዮጵያ ነገ ዜና || የኮሮና ቫይረስን በወረርሽኝ መከሰትን ተከትሎ ለመከላከሉና ለሕክምናው ተግባር የሚያገለግሉ መሣሪያዎች ደረጃ ዳግም እየተከለሰ እንደሆነ ተነገረ።

ከዚህ በፊት ጥቅም ላይ የዋሉ፣ ዳግም የተከለሱ፣ እንዲሁም አዲስ የተዘጋጁ 28 ደረጃዎች ከቫይረሱ መከሰት በኋላ ይፋ መሆናቸውን ሠምተናል።

የኢትዮጵያ ደረጃዎች ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር አቶ እንዳለው መኮንን ለሚገቡ ምርቶችም የዓለም ጤና ድርጅት መመሪያን መሠረት ያደረጉ ደረጃዎች መዘጋጀታቸውን ዛሬ ገልፀዋል።

በመሆኑም ከውጭ የሚገባ ሳኒታይዘር የዓለም ጤና ድርጅትን መመሪያ መሠረት ያደረገውን ደረጃ የግድ ማሟላት እንዳለበት፣ ከአፍ መሸፈኛ ወይም ማስክ ጋር በተገናኘም ሠባት የአውሮፓ ደረጃዎች የኢትዮጵያም ሆነው እንዲያገለግሉ መወሰኑን አስታውቀዋል።

የኮሮና ቫይረስ በወረርሽኝ መልክ መከሰትን ተከትሎ አዲስ የወጡ፣ የተከለሱ፣ እንዲሁም ከዓለም ጤና ድርጅትና የአውሮፓ ሀገራት ተወስደው፤ ለኢትዮጵያም እንዲያገለግሉ የተወሰኑ ደረጃዎች ብዛት በአጠቃላይ 38 እንደሆኑ ተነግሯል።

እነዚህን ደረጃዎች ያላሟሉ የኮሮና ቫይረስ መከላከያና ሕክምና መሣሪያዎች ወደ ሀገር ውስጥ መግባት አይችሉም የተባለ ሲሆን፣ ወደ ውጪ መላክ የሚፈልጉ የሀገር ውስጥ አምራቾችም በተመሳሳይ ደረጃዎቹን ማሟላት እንዳለባቸው ተገልጿል።

LEAVE A REPLY