ኢትዮጵያ ነገ ዜና || በሀገራችን ኢትዮጵያ ባለፉት 24 ሰዐታት ውስጥ ለ 1,047 ሰዎች በተደረገ የላቦራቶሪ ምርመራ አምስት (5) ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያቸው ተረጋገጠ፡፡ ይህን ተከትሎም በአጠቃላይ በሀገራችን በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥር መቶ አርባ አምስት (145) ሊደርስ ችሏል።
የጤና ጥበቃ ሚኒስትር ይፋ ባደረገው የታማሚዎች ዝርዝር መሠረት:- ታማሚ 1 – የ75 ዓመት ኢትዮጵያዊት የአዲስ አበባ ነዋሪ ፤ የውጭ ሀገር ጉዞ ታሪክ የሌላቸውና በበሽታው ከተያዘ ሰው ጋር ያላቸው ግንኙነት በመጣራት ላይ ያለ (በጤና ተቋም ተኝተው ከሚታከሙ ህሙማን ከተወሰደ ናሙና የተገኘ)
ታማሚ 2 – የ25 ዓመት ኢትዮጵያዊ ፣ የመኖሪያ ቦታ አፋር፤ ከጅቡቲ የተመለሰና በአፋር አስገዳጅ ለይቶ ማቆያ ውስጥ ያለ።
ታማሚ 3 – የ22 ዓመት ኢትዮጵያዊ ፤ የመኖሪያ ቦታ አፋር ፤ ከጅቡቲ የተመለሰና በአፋር አስገዳጅ ለይቶ ማቆያ ውስጥ የሚገኝ።
ታማሚ 4 – የ8 ዓመት ኢትዮጵያዊት የአዲስ አበባ ነዋሪ፤ የውጭ ሀገር ጉዞ ታሪክ የላትም፤ በበሽታው ከተያዘ ሰው ጋር ግንኙነት ያላት።
ታማሚ 5 – የ19 ዓመት ኢትዮጵያዊት የመኖሪያ ቦታ ኦሮሚያ፣ ባቱ ፤ የውጭ ሀገር የጉዞ ታሪክ የሌላት፤ በበሽታው ከተያዘ ሰው ጋር ግንኙነት ያላት መሆናቸውን አስፍሯል::
ይህ በእንዲህ እንዳለ በትላንትናው ዕለት 16 ሰዎች (15 ከአዲስ አበባ እና 1 ከአማራ ክልል) ከበሽታው ሙሉ ለሙሉ ያገገሙ ሲሆን፤ በአጠቃላይ በሀገራችን ከበሽታው ያገገሙ ሰዎች ቁጥር ዘጠና አንድ (91) እንደደረሰ ለማወቅ ተችሏል።