ግብፅ ለፀጥታው ም/ቤት ስሞታ ብታቀርብም ኢትዮጵያ አቋሟን እንደማትቀይር ገለፀች

ግብፅ ለፀጥታው ም/ቤት ስሞታ ብታቀርብም ኢትዮጵያ አቋሟን እንደማትቀይር ገለፀች

ኢትዮጵያ ነገ ዜና || ግብፅ ከታላቁ የህዳሴ ግድብ የውሃ ሙሌት ጋር በተገናኘ ያቀረበችውን ስሞታ እና ለፀጥታው ምክር ቤት የሰደደችውን ደብዳቤ የኢትዮጵያ መንግሥት እንደተመለከተው የውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡

ግብፅ ይህን ትበል እንጂ ኢትዮጵያ ምንም ዓይነት የአቋም ለውጥ እንደማታደርግ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ዳግም ይፋ አድርጓል፡፡ ኢትዮጵያ ይህን ጉዳይ በሦስቱ አገሮች በጋራ ውይይት ይፈታል የሚል አቋም ነው ያላት፡፡

ሀገራቱ እስከ ዛሬ በነበራቸው ውይይት ላይ ኢትዮጵያ አስፈላጊውን ሁሉ ስታደርግ ነበር ያሉት በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የቃል አቀባይ ፅ/ቤት ተጠባባቂ ዋና ቃል አቀባይ አቶ አምሳሉ ትዕዛዙ፤ ግብፅ ጉዳዩን ወደ ተባበሩት መንግሥታት ብትወስደውም የኢትዮጵያ መንግሥት ይህ አካሄድ ይጠቅማል ብሎ አያስብም ሲሉ አስረግጠው ተናግረዋል::

LEAVE A REPLY