አስቸኳይ አዋጁን በመተላለፍ ሰርግ የደገሰው ግለሰብ መቀጣቱ ተሰማ

አስቸኳይ አዋጁን በመተላለፍ ሰርግ የደገሰው ግለሰብ መቀጣቱ ተሰማ

ኢትዮጵያ ነገ ዜና || መንግሥት ያወጣውን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅን በመተላለፍ ሰርግ የደገሰው ግለሰብ መቀጣቱ ተነገረ።

ግለሰቡ የተቀጡት በኦሮሚያ ከልል በምስራቅ ሸዋ ዞን፣ ግንቢቹ ወረዳ የኮሮና ቫይረስን ለመከላከል የወጣውን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅን በመተላለፍ ሰርግ በመደገሱ መሆኑ ተገልጿል፡፡

በዚህ መሠረት ግለሰቡ የተቀጣው በአንደ ቦታ ከአራት ሰው በላይ በመሰብሰብ ፣ ልጁን ለመዳር ሰርግ በመደገሱ ነው::ግለሰቡ በድግሱ ላይ በርካታ አጃቢዎችና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶችን ጋብዞም ነበር  ።

የድርጊቱ ባለቤት የሆነው ግለሰብ ተይዞ የግንቢቹ ወረዳ ፍርድ ቤት ዛሬ በዋለው ችሎት 2 000 ብር እንዲቀጣ የወሰነበት መሆኑ ታውቋል:: መንግሥት የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ቢያወጣም ህጉን የተላለፉ ሰዎች እስካሁን ድረስ በተለያዮ ከተሞች ሁለት ሺኅ እና ሦስት ሺኅ ብሮችን ብቻ እንዲቀጡ መደረጉ በብዙኃኑ ኅብረተሰብ ዘንድ ቅሬታን እየፈጠረ ይገኛል::

LEAVE A REPLY