በኢትዮጵያ ከፍተኛው ቁጥር ተመዘገበ ፣ 25 ሰዎች በአንድ ቀን በኮሮና ተያዙ

በኢትዮጵያ ከፍተኛው ቁጥር ተመዘገበ ፣ 25 ሰዎች በአንድ ቀን በኮሮና ተያዙ

ኢትዮጵያ ነገ ዜና || ባለፉት ሀያ አራት ሰዐታት ውስጥ በተደረገው 1 ሺህ 847 የላብራቶሪ ምርመራ 25 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ተገኝቶባቸዋል። ዛሬ የተመዘገበው ቁጥር ቫይረሱ በኢትዮጵያ ከተከሰተ ወዲህ ከፍተኛው ሆኗል።

ቫይረሱ ከተገኘባቸው ሰዎች ውስጥ 19 ሰዎች ምንም ዓይነት የውጭ ሀገር የጉዞ ታሪክ እና ቫይረሱ ከተገኘባቸው ሰዎች ጋር ንክኪ የሌላቸው መሆናቸውን  የገለፁት ጤና ሚኒስትሯ ዶክተር ሊያ ታደሰ፤ ከቀሪዎቹ ሥድስት ሰዎች መሀል ሦስቱ ቫይረሱ ከተገኘባቸው ሰዎች ጋር ንክኪ ያላቸው ሲሆን፣ ቀሪዎቹ ሦስቱ ደግሞ የውጭ ሀገር የጉዞ ታሪክ ያላቸው መሆናቸውንም ይፋ አድርገዋል።

የኮቪድ 19 ቫይረስ የተገኘባቸው ሁሉም ኢትዮጵያውያን ሲሆኑ ፤ እድሜያቸው ከ17 እስከ 65 ዓመት የሆኑ 24 ወንዶች እና አንዲት ሴት መሆናቸው ታውቋል።

ቫይረሱ የተገኘባቸው ሰዎች መኖሪያ 21 በአዲስ አበባ፣ 2 ደበቡብ ክልል ሃድያ ከንባታ ዞን፣ 2 በኦሮሚያ ክልል (በቦረና ለይቶ ማቆያ እና በፊንፊዜ ዙሪያ ልዩ ዞን) መሆኑንም የጤና ሚኒስትሯ አስታውቀዋል። በዚህ መሠረት አሁን ላይ በአጠቃላይ በኢትዮጵያ ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር 187 ደርሷል።

LEAVE A REPLY