ኢትዮጵያ ነገ ዜና || መንግሥት ለአነስተኛና መካከለኛ ኢንዱስትሪዎች 4.5 ቢሊየን ብር ብድር ፈቅጃለሁ አለ። ኢንዱስትሪዎቹ የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ባሳደረው ተፅዕኖ እንዳይጎዱ በመንግሥት በኩል ድጋፍ እንዲደረግላቸው የሚጠይቅ ጥናት ለመንግሥት ቀርቦ እንደነበር ይታወሳል።
ጥናቱ የታክስ እፎይታና የብድር አቅርቦት በመንግሥትበኩል የሚመቻችላቸውና የገበያ ትስስር እንዲፈጠርላቸውይጠይቃል፡፡ ጥያቄዎቹ ሙሉ በሙሉ በመንግሥት እንደ ተመለሱ የአነስተኛና መካከለኛ ኢንዱስትሪዎች ልማት ማስፋፊያ ባለሥልጣን የኮሚዩኒኬሽን ዳይሬክተር አቶ አሸናፊ መለሰ ዛሬ ተናግረዋል::
ከተመለሱት ጥያቄዎች አንዱና ዋነኛው የብድር አቅርቦት ነው ያሉት ዳይሬክተሩ ፤ ኢንዱስትሪዎቹ 4.5 ቢሊየን ብር የሥራ ማስኬጂያ ብድር ገንዘብ እንደ ተፈቀደላቸው አብራርተዋል ፡፡
አስቀድሞ ተጠይቆ የነበረው ብድር 3 ቢሊየን ብር ቢሆንም ፣ ልማት ባንክ 1.5 ቢሊየን ብር በመጨመር 4.5 ቢሊየን ብር እንደ ፈቀደ የጠቆሙት አቶ አሸናፊ መለሰ፤ በሀገራችን 19.000 የሚጠጉ አነስተኛና መካከለኛ ኢንዱስትሪዎች እንዳሉ ይፋ አድርገዋል::
ኢንዱስትሪዎቹ ከግማሽ ሚሊየን ለሚበልጡ ዜጎች የሥራ እድል መፍጠራቸውና ከአገር ውስጥ ምርት የ6.6 በመቶ ድርሻ አላቸወ። አጠቃላይ ካፒታላቸው ደግሞ ከ15 ቢሊየን ብር በላይ ነው ተብሏል፡