ኢትዮጵያ 25 የኮሮና ላብራቶሪዎቼን 52 ለማድረስ አቅጃለሁ አለች

ኢትዮጵያ 25 የኮሮና ላብራቶሪዎቼን 52 ለማድረስ አቅጃለሁ አለች

ኢትዮጵያ ነገ ዜና፡- ኢትዮጵያ የኮሮና ቫይረስ በተለያዮ ሀገራት ከተከሰተበት ጊዜ አንስቶ የተለያዮ ናሙናዎችን ወደ ውጭ ሀገራት ልካ ከማስመርመር የራሷ የሆኑ በርካታ አስተማማኝ ላብራቶሪዎችን ለመገንባት ችላለች ተባለ::

የኮሮና ቫይረስ መከሰቱ እንደተሰማ ኢትዮጵያ ወደ ውጪ ናሙና በመላክ ነበር በምርመራ የምታረጋግጠው፡፡ ዛሬ ላይ ግን በቀን 6,000 ናሙና የመመርመር አቅም ላይ ደርሻለሁ ነው ስትል ገልጻለች፡፡

በአሁኑ ሰዐት ኢትዮጵያ ውስጥ  ጥራታቸውን የጠበቁ ፣ የኮቪድ 19 ቫይረስን በተገቢው መንገድ መመርመር የሚያስችሉ ሀያ አምስት ላብራቶሪዎች አሏት:: ዛሬ 25 ደርሰዋል የተባሉ ላብራቶሪዎቿን ወደ 52 ለማሳደግ እየሠራሁ ነው ያለችው ኢትዮጵያ፤ ከዚህ በኋላ በለይቶ ማቆያ ውስጥ ሰዎች ከ14 ቀን በላይ አይቆዩም ስትል የቀደሙ የተዝረከረኩ አሠራሮቿን እንደምታስተካክል አስታውቃለች፡፡

በተያያዘ ዜና ኢትዮጵያ ውስጥ ባለፉት ሀያ አራት ሰዐታት ውስጥ  ለ2424 (ሁለት ሺኅ አራት መቶ ሀያ አራት)  ሰዎች በተደረገ የለብራቶሪ ምርመራ  ዐሥራ አንድ ሰዎች የኮቪድ 19 ቫይረስ እንደተገኘባቸው የጤና ጥበቃ ሚኒስቴር ገልጿል::

LEAVE A REPLY