ኢትዮጵያ ነገ ዜና፡- የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሠራተኛ የሆነች አንዲት ሴት በሥራ ባልደረባዋ ከኋላዋ በጥይት ተመትታ ሕይወቷ ማለፉ ተነገረ::
በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በተለምዶ “ቴድሮስ አደባባይ” ተብሎ የሚጠራው የባንኩ ቅርንጫፍ የጥበቃ ሠራተኛ የነበረችው ሴት ከወንድ ባልደረባዋ በተተኮሰባት ጥይት ህይወቷ ማለፉ ተረጋግጧል፡፡
ሁለቱ የሥራ ባልደረቦች ከሥራ ውጭ ያላቸውን ግንኙነት በተመለከተ መረጃዎችን ለማግኘት ጥረት ያደረገው የአዲስ አበባው የኢትዮጵያ ነገ ዘጋቢ ገዳይና ሟች በጣም ይቀራረቡ እንደነበር ከታማኝ ምንጮች ጥቆማ ደርሶኛል ብሏሌ::
አሁን ላይ ለግድያ ያበቃው ጉዳይ ምን እንደሆነ ማረጋገጥ ባይቻልም ረዘም ላሉ ደቂቃዎች ሁለቱ የጥበቃ ሠራተኞች ሲጨቃጨቁና ኃይለ ቃል ሲለዋወጡ ነበር ተብሏል::
የጥበቃ ሠራተኛዋ ሕይወት ሊያልፍ የቻለው ከባልደረባዋ በተተኮሰ ጥይት ጀርባዋ ላይ በመመታቷ ነው:: የተኩስ ድምፁን ተከትሎ የባንኩ ሠራተኞችና በአካባቢው የነበሩ ሰዎች ሕይወቷን ለማትረፍ በአፋጣኝ ወደ ህክምና መስጫ ተቋም ቢወስዷትምም ህይወቷን ለማትረፍ ሳይቻል ቀርቷል፡፡ የሥራ ባልደረባው ላይ ግድያ የፈጸመውን የባንኩን ዘበኛ ፖሊስ በቁጥጥር ስር አውሎት ጉዳዮን እያጣራ ይገኛል፡፡