አራት የምሥራቅ አፍሪካ መሪዎች በወቅታዊው የቀጠና ጉዳዮች ላይ እየመከሩ ነው

አራት የምሥራቅ አፍሪካ መሪዎች በወቅታዊው የቀጠና ጉዳዮች ላይ እየመከሩ ነው

ኢትዮጵያ ነገ ዜና፡- ከምሥራቅ አፍሪካ ማኅበረሰብ አባል ሀገራት መካከል የአራት ሀገራት መሪዎች በወቅታዊ ቀጣናዊ ጉዳዮች ላይ እየመከሩ ነው ተባለ::

የአራቱ ሀገራት መሪዎች በወቅታዊ ቀጣናዊ ጉዳዮች ላይ ፣ በቪዲዮ ኮንፍራንስ በጋራ የመከሩት የሩዋንዳ ፣ ዩጋንዳ ፣ኬንያና የደቡብ ሱዳን መሪዎች ናቸው፡፡

የወቅቱ የማኅበረሰቡ አባል ሀገራት ሊቀመንበር በሆኑት የሩዋንዳው ፕሬዚዳንት ፖል ካጋሜ ሰብሳቢነት መሪዎቹያካሄዱት ውይይት የድንበር ተሻጋሪ ንግድና የኮሮና ወረርሽኝን በተመለከተ መሆኑ ተነግሯል፡፡

ሀገራቱ በመካከላቸው የኖረው ድንበር ተሻጋሪ ንግድ ሳይቋረጥ የኮሮና ወረርሽኝን መዛመት በጋራ መቆጣጠር ስለሚችሉባቸው አማራጮች ላይ በጥልቀት መወያየታቸውን ያስነበበው አፍሪካ ኒውስ ነው::

LEAVE A REPLY