ኢትዮጵያ ነገ ዜና፡- በኢትዮጵያ ባለፉት 24 ሰዐት ውስጥ ለ2.650 (ሁለት ሺኅ ሥድስት ሀምሳ) ሰዎች በተደረገ የላቦራቶሪ ምርመራ 2 ተጨማሪ ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ተገኝቶባቸዋል፡፡
ቫይረሱ እንደተገኘባቸው በምርመራ የተረጋገጠው ሁለቱ ሰዎች (ወንድ ኢትዮጵያዊያን)፣ የውጭ ሀገር የጉዞ ታሪክ ያላቸውና እድሜያቸውም 24 እና 33 መሆኑን የገለፁት የጤና ሚኒሴትሯ ዶክተር ሊያ ታደስ ፤ አንዱ ከትግራይ ክልል የድንበር ተሸጋሪ አሽከርካሪ እና መቐለ ለይቶ ማቆያ የነበረ፣ አንዱ ደግሞ ከሶማሌ ክልል ጅግጅጋ ለይቶ ማቆያ የነበረ መሆናቸውን አስታውቀዋል።
በሌላ በኩል ትላንት ተጨማሪ ሁለት ሰዎች ከበሽታው ያገገሙ ሲሆን ፤ በአጠቃላይ ከቫይረሱ ያገገሙ ሰዎች ቁጥር 108 ደርሷል:: በአጠቃላይ እስካሁንም 41 ሺኅ 698 የላቦራቶሪ ምርመራ መከናወኑን ሚኒስትሯ ጠቁመዋል።