በኩዌት መጠለያ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን መንግሥት ወደ ሀገር ቤት እስኪመልሳችሁ ታገሱ ተባሉ

በኩዌት መጠለያ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን መንግሥት ወደ ሀገር ቤት እስኪመልሳችሁ ታገሱ ተባሉ

ኢትዮጵያ ነገ ዜና፡- እስኪየኮቪድ 19 ቫይረስ ያመጣውን ሁለንተናዊ ጣጣ  ተከትሎ በስደት ያሉ ኢትዮጵያውያን በሰው ሀገር ለችግር መጋለጣቸውን ተከትሎ፣ በኩዌት በመጠለያ የምትገኝ ኢትዮጵያዊያን ወደ ሀገራቸው እስከትሳፈሩ ድረስ በትዕግስት እንዲጠብቁ መንግሥት አሳሰበ ።

“የኩዌት የመኖሪያ ፈቃድ ህግ ተላልፋችሁ ፣ የሀገሪቱ መንግሥት የሰጠውን የምህረት አዋጅ መጠቀምን አስመልክቶ ኤምባሲው የጉዞ ሰነድ ሰርቶላችሁ በመጠለያ ያላችሁ ኢትዮጵያውያን ታገሱ”  የሚለውን መልዕክት ያስተላለፈው በኩዌት የሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ ነው፡፡

ከኩዌት እና ከሚመለከታቸው ጋር በየግዜው እየተነጋገረ መሆኑን ጠቁሞ፤ ዜጎች ወደ ሀገር ቤት እስከምትሳፈሩ ድረስ በትዕግስት በመጠበቅ፣ ከተሳሳተ እና ከውሸት መረጃ ተጠበቁ፣ አስፈላጊውንም መረጃ ከኤምባሲው የመረጃ መረብ ተመልከቱ ሲል ምክር ለግሷል፡፡

LEAVE A REPLY