ቅዱስ ሲኖዶስ በቤተ ክርስቲያናት የተቋረጠው መንፈሳዊ አገልግሎት እንዲጀመር ወሰነ

ቅዱስ ሲኖዶስ በቤተ ክርስቲያናት የተቋረጠው መንፈሳዊ አገልግሎት እንዲጀመር ወሰነ

ኢትዮጵያ ነገ ዜና፡- በኮቪድ 19 ወረርሽኝ ምክንያት በየአጥቢያ ቤተክርስቲያናት ተቋርጦ የቆየው መንፈሳዊ አገልግሎቶች ዳግም እንዲጀመር ቅዱስ ሲኖዶስ ውሳኔ አሳለፈ።

ቤተ ክርስቲያን ዳግም ወደ መደበኛ መንፈሳዊ አገልግሎት ስትመለስ፤ የሃይማኖት አባቶች፣ በየሰንበት ትምህርት ቤቱ ያሉ ወጣቶች የማስተባበሩን ሥራ እንዲከውኑ አዟል፡፡

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ ምዕላተ ጉባኤ ከግንቦት አራት ጀምሮ ሲያካሂድ የቆየውን ጉባኤ ካጠናቀቀ በኋላ በሰጠው መግለጫ፤ በወረርሽኙ ምክንያት በየአጥቢያ ቤተ ክርስቲያኑ መንፈሳዊ አገልግሎቶች መቋረጣቸው በምዕመናን ሕይወት ላይ ችግር  መፍጠሩን ይፋ አድርጓል፡፡

ምዕመናን ከቤተክርስቲያን ተለይተው መኖር  አይችሉም ያለው የቅዱስ ሲኖዶስ መግለጫ፤ ከአሁን በኋላ አገልግሎቶቹ ዳግም ተጀምረው፣ የጤና ባለሙያዎች በሚሰጡት ምክር መሰረት አካላዊ ርቀትን ጠብቀው አገልግሎቱ እንዲሰጥ ውሳኔ አሳልፏል፡፡

የትኞቹ አገልግሎቶች ዳግም እንደሚጀመሩ በግልፅ ያላስቀመጠው የቅዱስ ሲኖዶስ መግለጫ፤ በተለያዩ የፖለቲካ ድርጅቶች መካከል እየታየ ያለው አለመግባባትና የቃላት መወራወር በአጭሩ ካልተገታ፣  እንዲሁም መፍትኄካልተበጀለት ተጨማሪ አገራዊ ቀውስ ሊያስከትል እንደሚችል ስጋቱን ገልጾ፤ የፖለቲካ ድርጅቶች ሁሉ ለአገራዊ ሰላምና ለሕዝባዊ አንድነት በጋራ ሊቆሙ ይገባል ሲል መክሯል፡፡

LEAVE A REPLY