የኢትዮጵያ አየር መንገድ በማክስ 737 አውሮፕላን ለደረሰበት ኪሳራ ቦይንግን ዘግይቶ ካሳ ጠየቀ

የኢትዮጵያ አየር መንገድ በማክስ 737 አውሮፕላን ለደረሰበት ኪሳራ ቦይንግን ዘግይቶ ካሳ ጠየቀ

ኢትዮጵያ ነገ ዜና፡- የኢትዮጵያ አየር መንገድ ባለፈው ዓመት መጋቢት ወር ላይ ከተከሰተው የቦይንግ 737 ማክስ አውሮፕላን አደጋ ጋር በተያያዘ ለደረሰበት ኪሳራ ፣እንዲሁም አደጋው በመልካም ስምና ዝናው ላይ ላደረሰበት ጉዳት ካሳ እንዲከፈለው ለአውሮፕላኑ አምራች ኩባንያ ጥያቄ አቀረበ፡፡

የአየር መንገዱ የቦይንግ ምርቶች የሆኑት 737 ማክስ አውሮፕላኖች አደጋው መከሰቱን ተከትሎ፣ ከቴክኒክ ብልሽት ጋር በተያያዘ ከበረራ በመታገዳቸውና ሥራ ፈትተው በመቆማቸው እንዲሁም፣ የግዢ ስምምነት የፈጸመባቸውን ሌሎች አውሮፕላኖች በወቅቱ ሊያስረክበው ባለመቻሉ ሳቢያ ለደረሰበት ኪሳራ፣ ማግኘት ሲገባው ላጣው ገቢ ካሳ እንዲከፍለው ለቦይንግ ኩባንያ የኢትዮጵያ አየር መንድ ጥያቄ ማቅረቡን የዘገበው ርይተርስ ነው::

አየር መንገዱ ተገቢውን ጥያቄ ማቅረቡንና ክፍያው እስከ ሰኔ ወር መጨረሻ ይፈጸምልኛል ብሎ እንደሚጠብቅ የአየር መንገዱ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ተወልደ ገብረ ማርያም መናገራቸውም ተሰሜቷል፡፡

ከሌሎች የአፍሪካ ሀገራት አየር መንገድ በተሻለ ጥሩ እየተንቀሳቀሰ ይገኛል የሚባልለትየኢትዮጵያ አየር መንገድ፤ ለቦይንግ ኩባንያ ምን ያህል ገንዘብ በካሳ መልክ እንዲከፈለው እንደጠየቀ በግልፅ የተቀመጠ ነገር የለም፡፡

LEAVE A REPLY