790 ሚሊዮን ብር የወጣበት የቃሊቲ የአውቶቢስ ዴፖ ዛሬ ተመረቀ

790 ሚሊዮን ብር የወጣበት የቃሊቲ የአውቶቢስ ዴፖ ዛሬ ተመረቀ

ኢትዮጵያ ነገ ዜና፡-  በ790 ሚሊየን ብር ወጪ የተገነባው የቃሊቲ የአውቶብስ ዴፖ ዛሬ መመረቂ ተሰማ:: የአውቶብስ ዴፖውን የአዲስ አበባ ምክትል ከንቲባ ኢንጂነር ታከለ ኡማ በይፋ መርቀው ለአገልግሎት ክፍት መሆኑን አብስረዋል።

5 ነጥብ 2 ሄክታር ስፋት ያለው የቃሊቲ የአውቶብስ ዴፖ ማዕከል በውስጡ ለአውቶብሶች በቴክኖሎጂ የተደገፈ የጋራዥ አገልግሎት፣ የእጥበትና የነዳጅ አቅርቦት ከመስጠት ባሻገር፤ ዘመናዊ የአስተዳደር ህንጻ ያለው ሲሆን፤ በአንድ ጊዜ ከ250 እስከ 300 አውቶብሶች ከምድር በላይ እና 85 አውቶብሶችን ከምድር በታች መያዝ የሚችል መሆኑ በምረቃ ሥነ ሥርዓቱ ላይ ተገልጿል።

ግዙፉ ዴፖ ዐሥራ ሁለት ዘመናዊ የመኪና ማጠቢያዎች፣ አራት ዘመናዊ የነዳጅ ማደያዎች እና  ዘመናዊ ጋራዥ በውስጡ የያዘ ሲሆን፤ የደህንነት ካሜራዎች የተገጠሙለት ዴፖው በአንድ ቦታ ስምሪት የሚሰጥ ማዕከልንም አካትቷል።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሥራ አስኪያጅ ኢንጂነር አወቀ ኃይሌ፣ ዴፖው አስተዳደሩ በቀጣይ ለሚገዛቸው 3 ሺኅ አውቶቢሶች አገልግሎት እንደሚሰጥ የገለፁት ከንቲባ ታከለ ኡማ፤ የአውቶቢስ ዴፖውን በቀጣይ ለማስፋፋት ከጎኑ ለዚሁ አገልግሎት የሚውል ሁለት ሄክታር መሬት መከለሉን አስታውቀዋል።

የቃሊቲው ዴፖ ፕሮጀክት በከተማ አስተዳደሩ የተጀመሩ ፕሮጀክቶችን የመጨረስ ግብ አንድ አካል መሆኑን ያመላከቱት ከንቲባው፤ በከተማዋ አስተዳደሩ እየተገነቡ ያሉ እና የሚገነቡ ፕሮጀክቶች መካከለኛ እና ዝቅተኛ ገቢ ያላቸው ዜጎችን ተጠቃሚነት ላይ የተመረኮዙ ናቸው ብለዋል::

LEAVE A REPLY