ኢትዮጵያ ነገ ዜና፡- የሕገ መንግሥት ጉዳዮች አጣሪ ጉባዔ የሕገ መንግሥት ትርጉምን በተመለከተ ያዘጋጀው የባለሙያዎች ሐሳብ መስጫ መድረክ ዛሬ ተጀምሯል።
ጉባዔው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት፤ በሕገ መንግሥታዊ ጉዳዮች ላይ ለቀረበለት ጥያቄ የሚመለከታቸው ተቋማት እና ባለሙያዎች አስተያየት እንዲያቀርቡ ጥሪ ማድረጉን ተከትሎ ነው ዛሬ በሸራተን ሆቴል ውይይት እየተካሄደ ያለው።
በዚህም መሠረት ከሕገ መንግሥት ትርጓሜና ተያያዥ ጉዳዮች ጋር ባለሙያዎች ሐሳባቸውን መስጠት ጀምረዋል፤ በሐሳብ መስጫ መድረኩ ላይ የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዚዳንት ወይዘሮ መዓዛ አሸናፊን ጨምሮ ከተለያዩ ተቋማት የተውጣጡ ባለሙያዎች ተሳታፊ ሆነዋል።
በውይይት መድረኩ ከሕገ መንግሥት ትርጓሜ ጋር በተያያዘ ባለሙያዎች ሠፋ ያለ ማብራሪያ ሰጥተዋል መባሉንም ሰሜተናል። የመድረኩ ተሳታፊዎች በቀረቡት ሐሳብና ማብራሪያዎች ላይ ጥያቄዎችን አቅርበው ከባለሙያዎች ምላሽ የተሰጠ ሢሆን የመጨረሻ የመግባቢያ ውሳኔውና የሕገ መንግሥት ውሳኔው በቅርብ ጊዜ ውስጥ ለሕዝብ ይፋ ይሆናል ተብሎ ይጠበቃል።