የኮሮና ቫይረስ እያለብኝ ገንዘብ ከፍዬ ከለይቶ ማቆያ ወጥቻለሁ ያለው ግለሰብ ተቀጣ

የኮሮና ቫይረስ እያለብኝ ገንዘብ ከፍዬ ከለይቶ ማቆያ ወጥቻለሁ ያለው ግለሰብ ተቀጣ

ኢትዮጵያ ነገ ዜና– በደቡብ ወሎ ዞን የቃሉ ወረዳ ፍርድ ቤት በውሸት የኮሮና ቫይረስ እያለብኝ ከለይቶ ማቆያ በገንዘብ ወጣሁ ያለ ግለሰብ በፍርድ ቤት ተቀጣ።

ግለሰቡ የተሳሳተና ከእውነት የራቀ መረጃ ከመስጠቱ ባሻገር በነዋሪዎች ላይ ስጋት በመፍጠር ጭምር ፖሊስ በቁጥጥር ሥር አውሎ በሕግ ፊት እንዲቀርብ አድርጎታል ።

በሀሰት” ከአዲስ አበባ የለይቶ ማቆያ አምልጫለሁ” ያለውግለሰብ በ2 ዓመት እስራት ወይም በ4,000 ብር እንዲቀጣ ተወስኖበታል።

ደመቀ ሙሄ የተባለው ግለሰብ “ከአዲስ አበባ ለይቶ ማቆያ አምልጨ ነው የመጣሁት ፤ ከእኔ ጋርም  የወጣነው 13 ሰዎች ነን ፣ አንዱ ጓደኛችን በኮሮና ቫይረስ ሕይወቱ አልፏል። እኔ ራሴ የኮሮና ቫይረስ አለብኝ፤ ሁላችንም ከማቆያው ብር ከፍለን ነው የወጣነው” በማለት ያወራውን ሀሰተኛ ወሬ ዳግም ፍርድ ቤት ቀርቦ በማመኑ ሊቀጣ ችሏል።

ፖሊስ ግለሰቡ ያላቸው ነገሮች በሙሉ ከእውነት የራቁና ሀሰት መሆኑን በምርምራ ማጣራቱን  ጠቁሞ ግለሰቡምበተደረገለት ምርመራ ከኮሮና ቫይረስ ነጻ መሆኑንም አረጋግጫለሁ ብሏል።

LEAVE A REPLY