ዛሬ ሌሊት በባህርዳር ሁለት ሰፈሮች የእሳት አደጋ ደረሰ

ዛሬ ሌሊት በባህርዳር ሁለት ሰፈሮች የእሳት አደጋ ደረሰ

ኢትዮጵያ ነገ ዜና– በባህር ዳር ሁለት ሠፈሮች ዛሬ ሌሊት በመኖሪያ ቤቶችና ሱቆች ላይ ከፍተኛ የእሳት አደጋ መድረሱ ተነገረ።

በንብረት ላይ ከፍተኛ ጉዳት አደጋው የደረሰው ቀበሌ 8 በሚገኝ የመኖሪያ ቤት እና ቀበሌ 12 አካባቢ በሚገኙ የሞባይል መሸጫ የገበያ ማዕከላት ላይ ነው ተብሏል፡፡

በተለምዶ ቀበሌ ስምንት ተብሎ ከሚጠራው አካባቢ ከሌሊቱ 5፡50 ላይ ከአንድ መኖሪያ ቤት የተነሳ እሳት፣ መኖሪያ ቤቱ ሙሉ በሙሉ እንዲወድም ከሚድረጉ ባሻገር፤ ከጎረቤት ያለ ሌላ ቤት ላይ መጠነኛ ጉዳት እንዲደርስ ምክንያት መሆኑን የሚወጡ መረጃዎች ይጠቁማሉ ፡፡

የእሳት አደጋው በመኖሪያ ቤቶቹና በንብረት ላይ ጉዳት ከማድረሱ በቀር በሰው ሕይወትም ሆነ በአካል ላይ ያደረሰው ጉዳት አለመኖሩንም ፖሊስ አረጋግጧል::

በሌላ በኩል ቀበሌ 12 በሚገኘው የሞባይል የገበያ ማዕከል ላይም የእሳት ቃጠሎ ደርሷል።  በአደጋውም 48 ሱቆች ሙሉ በሙሉ ሲወድሙ፣ ሁለት የገበያ ማዕከላት ባሉት የሞባይል የገበያ ማዕከል የተነሳው እሳት፤ ሁሉንም ሱቆችና በውስጣቸው የነበረውን ንብረት አውድሟል፡፡

ወጣቶች፣ የፀጥታ ኃይል አባላት፣ የባሕር ዳር ከተማ አስተዳደር የእሳትና ድንገተኛ አደጋዎች መቆጣጠሪያና መከላከያ መኪና ደርሰው ወደ ሌሎች ሱቆችና ድርጅቶች ሳይስፋፋ እሳቱን መቆጣጠር መቻሉን አብመድ ዘግቧል፡፡

  የባሕር ዳር ከተማ አስተዳደር ፖሊስ መምሪያ የሚዲያና ኮሙዩኒኬሽን ክፍል ኃላፊ ዋና ኢንስፔክተር ታደሰ ዳኛቸውም የአደጋው መንስኤ እየተጣራ እንደሆነ አስታውቀዋል፡፡

LEAVE A REPLY