ኢትዮጵያ በክረምቱ 5 ቢሊዮን ችግኝ እተክላለሁ አለች

ኢትዮጵያ በክረምቱ 5 ቢሊዮን ችግኝ እተክላለሁ አለች

Ethiopia's Prime Minister Abiy Ahmed (C) arrives at Khartoum international airport on June 7, 2019. - Ethiopia's prime minister arrived in Khartoum today seeking to broker talks between the ruling generals and protesters as heavily armed paramilitaries remained deployed in some squares of the Sudanese capital after a deadly crackdown, leaving residents in 'terror'. (Photo by ASHRAF SHAZLY / AFP) (Photo credit should read ASHRAF SHAZLY/AFP/Getty Images)

ኢትዮጵያ ነገ ዜና– ያለፈውን ዓመት የክረምት ወር ችግኝ በአንድ ቢሊዮን ብልጫ በዘንድሮው ክረምት በኢትዮጵያ ለማስተከል ሽር ጉድ እያሉ የሚገኙት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የቢሾፍቱ ችግኝ ማፍያን ጎብኝተዋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በፌስ ቡክ ገጻቸው ባሰፈሩት ጽሑፍ  ላይ ፤ በመጪው ክረምት ለሚካሂደው የ5 ቢሊዮን ችግኞች “የአረንጓዴ አሻራ” መርሀ ግብር የሚደረገውን ዝግጅት መመልከታቸውን ጠቁመው ፤ ፕሪሲሽን ቴክኖሎጂን በመጠቀም እስካሁን የተደረሰበት የክንውን ደረጃም በእጅጉ የሚደንቅ ነው ብለዋል፡፡

ፕሮጀክቱ ኢትዮጵያን በአረንጓዴ ልምላሜ የማልበስ ግብን የሚደግፍ እንደሆነ ያስነበቡን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የዘንድሮው የክረምት ወራት የአረንጓዴ አሻራ መርሀ ግብር በተያዘለት የጊዜ ሰሌዳ እንደሚከናወንም አረጋግጠዋል::

ያለፈው ዓመት የችግኝ ተከላ ፕሮግራም ኢትዮጵያ በአንድ ቀን 300 ሺኅ ያህል ችግኞችን በመትከል በህንድ ተይዞ የነበረውን የ76 ሺኅ ሪከርድ እንደሰበረች መንግሥት ቢገልፅም ፤ የጊነስ ወርልድ አዘጋጅች ግን የተመዘገበ የሪከርድ ለውጥ አለመኖሩን በመግለፅ የኢትዮጵያውያን ተስፋ ገደል ከትቶታል ።

ጊነስ ወርልድ “ኢትዮጵያ እንዲህ ዓይነት ዝግጅትና ሐሳብ ከነበራት ለእኛ ማሳወቅና ባለሙያዎችም መመደብ ነበረብን። ይህ ባልሆነበት ሁኔታ፣ እንዲሁ በደፈናው ሪከርድ ሰብሪያለሁ ማለት አይቻልም ። ዓለም ላይ እስካሁን የህንድን የችግኝ ተከላ ለመስበር የቻለ ሀገር የለም” ሲል መግለፁ አይዘነጋም::

LEAVE A REPLY