ኢትዮጵያ ነገ ዜና፡– የደቡብ ሱዳን ተቀዳሚ ምክትል ፕሬዝዳንት ዶክተር ሪያክ ማቻር እና የመከላከያ ሚኒስትር የሆኑት ባለቤታቸው በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተሰማ ።
ጥንዶቹ በኮቪድ 19 ቫይረስ መጠቃታቸው በምርመራ ከተረጋገጠ በኋላ ራሳቸው በመኖሪያ ቤታቸው ለይተው መቀመጣቸውም ተነግሯል።
ማቻር በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው የተረጋገጠው፣ ከአገሪቱ ብሔራዊ የኮሮና ቫይረስ ተከላካይ አካል ባልደረቦች ጋር ተገናኝተው ከተነጋገሩ በኋላ እንደሆነ የዘገበው ዘ ኢስት አፍሪካን፤ ከቢሯቸው ሠራተኞች እና ከጠባቂዎቻቸው መካከልም በኮሮና ቫይረስ የተያዙ መገኘታቸውን አስታውቋል ።
ባለትዳሮቹ ባለሥልጣናት ራሳቸውን በመኖሪያ ቤታቸው ወስነው የሚሰነብቱ ሲሆን ፤ በሐኪሞችም ክትትል ይደረግላቸዋል ነው የተባለው፡፡ በደቡብ ሱዳን 290 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ የተያዙ ሲሆን በበሽታው የአራት ሰዎች ሕይወት አልፏል፡፡