በአፋር 486 ሰዎች በለይቶ ማቆያ ጥበቃ እየተደረገላቸው ነው

በአፋር 486 ሰዎች በለይቶ ማቆያ ጥበቃ እየተደረገላቸው ነው

ኢትዮጵያ ነገ ዜና፡- በአፋር ክልል በአራት የለይቶ ማሰንበቻ (ማቆያ) ጣቢያዎች 486 (አራት መቶ ሰማኒያ ስድስት) ሰዎች ተለይተው ጥበቃ እየተደረገላቸው መሆኑ ተሰማ፡፡

በክልሉ በተለያየ አቅጣጫ በእግራቸው ጭምር ተጉዘው፣ ድንበር አሳብረው የሚገቡ ስደተኞች ቁጥር ከፍተኛ ነው። በቀን በአማካይ እስከ 350  (ሦስት መቶ ሀምሳ) ስደተኞች ከየመን እና ከጅቡቲ በግመልና በእግር ተጉዘው በህገ ወጥ መንገድ በኬላዎቹ እንደሚያልፉ መረጃዎች ይጠቁማሉ፡፡

የአፋር ክልል የወንጀል መከላከል ኮሚሽነንና የድንበር ጉዳዮች ሓላፊ ኮሚሽነር አህመድ አሪፍ እንደገለፁት ከሆነ፤ በኮሮና ቫይረስ ምክንያት ስደተኞቹ ከማኅበረሰቡ ጋር ከመቀላቀላቸው በፊት በማቆያዎች እንዲሰነብቱ የሚደረግ ሲሆን፣ አሁንም 480 ሰዎች በልዮ ሁኔታ ተለይተው ጥበቃ እየተደረገላቸው ይገኛል::

የአፋር ሕዝብ  የኮሮና ቫይረስን ሥርጭትን ለመቆጣጠር፤ ባህላዊ ዘዴዎችን ጭምር በመጠቀም የሳር ጎጆዎችን ቀልሶ ስደተኞቹን ለብቻቸው እያሰነበተ ይገኛል ተብሏል፡፡

LEAVE A REPLY