በመገናኛ ብዙኃን የሚቀርቡ የፈጠራ ውጤቶችን መንግሥት ሊሸልም ነው 

በመገናኛ ብዙኃን የሚቀርቡ የፈጠራ ውጤቶችን መንግሥት ሊሸልም ነው 

ኢትዮጵያ ነገ ዜና፡- በተለያዩ ዘርፎች የሚሠሩና በየመገናኛ ብዙኃኑ የሚቀርቡ የፈጠራ ውጤቶችን መርጦ መንግሥት ሊሸልም እንደሆነ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ገለፁ፡፡

መንግሥት በዚህ አስቸጋሪ ወቅት የሕዝብን ኑሮ ለማሻሻል የሚያስችሉ የተለያዩ የቴክኖሎጂና  የኪነ- ጥበብ ፈጣሪ ያላቸውን በረታታል በማለት በፌስ ቡክ ገጻቸው መልዕክት ያስተላለፉት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ፤ “የገበሬውን ምርታማነት ሊያሻሽሉ የሚችሉ የቴክኖሎጂ ፈጠራዎች፣ ግብርናን የሚያሻሽሉ፣ የፋብሪካ ምታማነትን የሚያሳድጉ፣ የንባብ ፍላጎትን የሚጨምሩ፣ በቀላሉ ማንኛውም ሰው በቤቱ ሆኖ ሊሠራቸው የሚችሉ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ፈጠራዎችን መንግሥት ያበረታታል ፣መርጦም ይሸልማል” ብለዋል፡፡

ለፈጠራ፣ ለአዳዲስ የቴክኖሎጂ ሙከራዎች፣ የቴክኒክ እውቀትን ለማሳደግ የሚረዱ ድርሰቶች፣ ሙዚቃዎች፣ ስዕሎች፣ አጫጭር ድራማዎችና ፊልሞች፤ እንዲሁም የሕዝብ አንድነት፣ የሀገር ፍቅር ስሜትን የሚያሳድጉ ጥበቦችና ፈጠራዎች ሌሎቹ የሚያሸልሙ ዘርፎች እንደሆኑም ጠቅላይ ሚኒስትሩ ገልፀዋል።

እንዲህ ዓይነቱ ለሀገርና ለሕዝብ የሚጠቅም ፈጠራዎች ያሏቸው እስከ መስከረም ወር ባለው ጊዜ በየመገናኛ ብዙኃኑ እንዲያወጡቸው ዶክተር ዐቢይ አሕመድ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡

LEAVE A REPLY