ዶክተር ስለሺ በቀለ በህዳሴው ግድብ ዙሪያ በአዲስ አበባ ለሚገኙ አምባሳደሮች ገለፃ አደረጉ

ዶክተር ስለሺ በቀለ በህዳሴው ግድብ ዙሪያ በአዲስ አበባ ለሚገኙ አምባሳደሮች ገለፃ አደረጉ

ኢትዮጵያ ነገ ዜና፡- ኢትዮጵያ በከፍተኛ ወጪ እየገነባች ያለችውን የህዳሴው ግድብ አስመልክቶ መቀመጫቸውን በአዲስ አበባ ላደረጉ (በከተማዋ ለሚገኙ) አምባሳደርች በቂ ማብራሪያ ሰጠች ።

ዛሬ በጉዳዮ ላይ ለአምባሳደሮቹ  ገለፃ  ያደረጉት የውሃ፣ መስኖ እና ኢነርጂ ሚኒስትር ዶክተር ኢንጂነር ስለሺ በቀለ መሆናቸው ታውቋል።

በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የስብሰባ አዳራሽ ውስጥ  በተካሄደው ገለጻ ላይ የታላቁ የህዳሴ ግድብ የግንባታ ሂደት እና በግድቡ ዙሪያ በኢትዮጵያ፣ ሱዳን እና በግብፅ መካከል ሲደረጉ የነበሩ ድርድሮች እንደተነሱና ሙያዊ ትንታኔ እንደተሰጠባቸው ተሰምቷል።

በግድቡ ዙሪያ በኢትዮጵያ፣ ሱዳን እና በግብፅ በአሜሪካ እና በዓለም ባንክ ታዛቢነት የተደረጉ ውይይቶች ለምን ስኬታማ አልሆኑም? የሚለው ላይ ዶክተር ኢንጂነር ስለሺ በቀለ ማብራሪያ ከመስጠታቸው ባሻገር ፤ የታላቁ ህዳሴ ግድብ በየትኛውም ሀገር ላይ ተጽዕኖ እንደማያደርስም አብራርተዋል ።

የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ግንባታ 73 በመቶ ደርሷል ያሉት ዶክተር ፣ ኢንጂነር ስለሺ ፤ ከፊታችን ሐምሌ ወር ጀምሮ ውሃ መያዝ እንደሚጀምርና ኢትዮጵያ ባወጣችው እቅድ መሠረት እንደምትጓዝ አስረግጠው ተናግረዋል።

LEAVE A REPLY