ግሎባል አልያንስ 11 ሚሊዮን ብር የሚያወጡ የሕክምና መሳሪያዎች ድጋፍ አደረገ

ግሎባል አልያንስ 11 ሚሊዮን ብር የሚያወጡ የሕክምና መሳሪያዎች ድጋፍ አደረገ

ኢትዮጵያ ነገ ዜና፡- ሁሌም ለሀገሩና ወገኑ የቻለውን ከማድረግ ወደ ኋላ የማይለውና በጭንቅ ጊዜ በፈጣን ደራሽነቱ የሚታወቀው አርቲስት ታናኝ በየነ ከመሰል ባልደረቦቹ ጋር ባቋመው ግሎባል አልያንስ አማካይነት ከዐሥራ አንድ ሚሊዮን ብር በላይ የሚያወጣ ድጋፍ አድርጓል።

የሰብዓዊ መብት  ተሟጋቹና ሀገር ወዳዱ አርቲስት ታማኝ በየነ የሚመራው ዓለም አቀፍ ትብብር ለኢትዮጵያውያን መብት (ግሎባል አሊያንስ ) በተሰኘው ድርጅት ያሰባሰበውን እና የኮሮና ቫይረስን ለመከላከል የሚያግዝ የ11.5 ሚሊዮን ብር የሚደርስ የሕክምና መሳሪያ ግብዓቶችን በዛሬው ዕለት ለሚመለከተው ተቋም ማስረከቡ ታውቋል።

ግሎባል አልያንስ የሕክምና መሣሪያዎቹን ለጤና ሚኒስትሯ ዶክተር ሊያ ታደሰ ባስረከበበት ወቅተ ይህ እርዳታ በውጭ ሀገራት ከሚገኙ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ለመጀመሪያ ዙር የተበረከተ አስቸኳይ እርዳታ መሆኑን የገለፁት የግሎባል አልያንስ አስተባባሪ አመሀ መኮንን፤ በሀገራችንም ሆነ በዓለም ሕዝብ ላይ የተጋረጠው የኮሮና ቫይረስ ሙሉ ለሙሉ እስኪወገድ ድረስ ግሎባል አልያንስ ኢትዮጵያውያንን በማስተባበር አስፈላጊውን ድጋፍ እንደሚያደርግም አረጋግጠዋል ።

LEAVE A REPLY