ኢትዮጵያ ፣ ግብፅና ሱዳን ያላቸውን ልዮነት እንዲፈቱ ጉተሬዝ አሳሰቡ

ኢትዮጵያ ፣ ግብፅና ሱዳን ያላቸውን ልዮነት እንዲፈቱ ጉተሬዝ አሳሰቡ

ኢትዮጵያ ነገ ዜና፡- የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ዋና ጸሐፊ አንቶኒዮ ጉተሬዝ ኢትዮጵያ፣ ግብፅ እና ሱዳን በታላቁ ህዳሴ ግድብ ዙርያ ያላቸውን ልዩነቶች ፤ ሰላማዊ በሆነና የጋራ ተጠቃሚነትን ባከበረ መልኩ እንዲፈቱ ጠየቁ።

ዋና ጸሐፊዉ በህዳሴ ግድብ ዙርያ የሚደረጉ  ድርድሮችን በቅርበት መከታተላቸውን እንደሚቀጥሉ ጠቁመው የእስካሁኑንም ሂደት የሚበረታታ ቢሆንም፣ በቀጣይም ሦስቱ ሀገራት  ድርድራቸውን እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር በ2015  በተፈራረሙት የመርሆች ስምምት መሠረት ሊቀጥሉ እንደሚገባ ምክር ለግሰዋል።

ከአምስት  ዓመት በፊት የተደረጉት የመርህ ስምምነቶች የጋራ ተጠቃሚነት፣ በቀና መንፈስ፣ ፍትሃዊነትን ባሰፈነ ሁኔታ እንዲሁም ዓለም ዐቀፍ ሕጎችን ዋና መሰረቱን ያደረገ መሆኑን ያስታወሱት አንቶኒዮ ጉተሬዝ፤ አገራቱ የፈረሙትን የመርሆች ስምምነት መሰረት ባደረገ መልኩ ያልተስማሙባቸው ጉዳዮችን ለመፍታት እንዲሠሩም ጠይቀዋል።

LEAVE A REPLY