ሕወሓት ሽሬ ዛሬ ከፍተኛ የሕዝብ ተቃውሞ ገጠመው

ሕወሓት ሽሬ ዛሬ ከፍተኛ የሕዝብ ተቃውሞ ገጠመው

ኢትዮጵያ ነገ ዜና፡- የትግራይ ሕዝብ በደደቢት ሽሬ አካባቢ የተቃውሞ እንቅስቃሴ መጀመሩ ታውቋል።

የትግራይ ወጣቶች በሀገር ምዝበራና በከባድና አሰቃቂ የሰብኣዊ መብት ጥሰቶች ተዘፍቆ የኖረው ወያኔን (ህወሓት) አስራ ሠባት ዓመት የትጥቅ ትግል ካደረገበት፣ በኋላም ሀገሪቱን ወደብ ያደረገ አሳፋሪ ስምምነት እንዲፈጽም ካስቻለው እና የትጥቅ ትግል ከጀመረበት ደደቢት ሽሬ አካባቢ ማንሳታቸው ታሪካዊ ግጥምጥሞሽ አሰጥቶታል።

ከቀን ቀን በትግራይ ክልል ውስጥ ህወሓት የሚያደርሰውን ተቃውሞ መሸከም ያቃታቸው የትግራይ ነዋሪዎች በትግራይ ክልል፣ በደደቢት ሽሬ የተቃውሞ ሰልፍ አድርገዋል::

አደባባይ የወጡትና ህወሓትን በመቃወም መንገዶች የዘጉት፣ የተለያዮ እንጨትና ጎማዎችን በማቃጠል በተቃውሞ ፍትህና ነፃነት ፈላጊ መሆናቸውን የገለፁት የትግራይ ወጣቶች የአስቸኳይ አዋጁን ተገን በማድረግ በፀጥታ ኃይሎች ስለተገደሉት ወጣቶችም ድምጻቸውን አሰምተዋል።

በሰልፉ ለተቃውሞ አደባባይ በወጡ ነዋሪዎችና በታጣቂዎች መሀል ከፍተኛ ግጭት መፈጠሩን የጠቆሙ ምንጮቻችን ይህ ዜና እስከተጠናከረበት ሰዐት ድረስ ትክክለኛ መረጃውን ለማግኘት ባይችሉም በፀጥታ ኃይሎች ጥቃት የተፈጸመባቸውና የታሰሪ ሰዎች መኖራቸውን ገልጸዋል።

LEAVE A REPLY