ኢትዮጵያ ነገ ዜና፡– በወጣቱ ፖለቲከኛ ነቢዮ ስሁል ሚካኤል የሚመራው የትግራይ ብልጽግና ፓርቲ፤ የአዲስ አበባ ከተማ ቅርንጫፉበይፋ ሥራ መጀመሩን አስታውቋል።
የህወሓት ተገዳዳሪ የሆነው የትግራይ ብልፅግና ፓርቲበይፋ ሥራ መጀመሩን በማስመልከት ከተለያዩ ክፍለ ከተሞች ከተውጣጡ አመራሮችና አባላት ጋር ውይይት አካሂዷል።
አባላቱና አመራሩ ቀድሞ የሕዝባዊ ወያኔ ሓርነት ትግራይ (ህወሓት) አባል የነበሩና አሁን የብልጽግናን ፓርቲ የተቀላቀሉ መሆናቸውም እየተነገረ ነው።
የውይይት መድረኩ ላይ የትግራይ ብልፅግና ፓርቲ ጽ/ቤትሓላፊ አቶ ነብዩ ስሁል ሚካኤልና ሌሎች አመራሮች በተገኙበት እንደተካሄደም ሰምተናል።