በኢትዮጵያ በአንድ ቀን ብቻ 61 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ ተያዙገኘባቸው

በኢትዮጵያ በአንድ ቀን ብቻ 61 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ ተያዙገኘባቸው

ኢትዮጵያ ነገ ዜና– ኢትየጵያ ውስጥ ባለፉት 24 ሰዐታት ውስጥ  ለ3 ሺኅ 757 ሰዎች በተደረገ የላብራቶሪ ምርመራ 61 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ እንደተገኘባቸው የጤና ሚኒስትር ገለፀ።

ይህን ከፍተኛ ቁጥር ተከትሎ በኢትዮጵያ ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው ሰዎች አጠቃላይ ቁጥር 494 ደርሷል፡፡
በተጠቀሱት ሰዐታት ቫይረሱ የተገኘባቸው ከ15 እስከ 70 እድሜ ክልል የሚገኙ ኢትዮጵያዊያን መሆናቸውን ሚኒስቴሩ አረጋግጧል።
ዛሬ ይፋ በሆነው መረጃ መሠረት ቫይረሱ ከተገኘባቸው ሰዎች መካከል ከፍተኛ መዘናጋት የሚታይባት ዋና ከተማዋ ከአዲስ አበባ 48 ሰዎች በማስመዝገብ ቀዳሚነቱን ይዛለች።
በሌላ በኩል 3 ሰዎች ከአፋር፣ 1 ሰው ከአማራ ክልል ፣ 7 ሰዎች ከሶማሌ ክልል እና 2 ሰዎች ከኦሮሚያ ክልል ሆነው ተመዝግበዋል።
ቫይረሱ የተገኘባቸው 11 ሰዎች የውጭ ሀገር ጉዞ ታሪክ ያላቸው፣ 5 ሰዎች በበሽታው ከተያዘ ሰው ጋር ንኪኪ ያላቸው ሲሆን 45 ሰዎች ግን ምንም ዓይነት የጉዞ ታሪክ እና በበሽታው ከተያዘ ሰው ጋር ግንኙነት የሌላቸው መሆኑን በዶክተር ሊያ ታደሰ የሚመራው የጤና ሚኒስትር ይፋ አድርጓል።
ኢትዮጵያ እስከአሁን ድረስ 76 ሺኅ 962 የኮሮና ቫይረስ ምርመራ ማድረጓንም ተነግሯል።

LEAVE A REPLY