በትግራይ በአብረሃ ደስታና የአምዶም ገ/ስላሴ ላይ ወከባና ጥቃት እየደረሱ ነው

በትግራይ በአብረሃ ደስታና የአምዶም ገ/ስላሴ ላይ ወከባና ጥቃት እየደረሱ ነው

ኢትዮጵያ ነገ ዜና– በትግራይ የሚደረገውን ሕዝባዊ እንቅስቃሴ ተከትሎ ህወሓት ትኩረት ያደረገባቸው የተፎካካሪ ፓርቲ አመራር እና አባሎችን ማገትና  ማሰር መጀመሩ ተነገረ።

“የጨለማው ዘመን ፣ ስውሩ ጠቅላይ ሚኒስትር” በሚባለው  ጌታቸው አሰፋ የሚመራው የትግራይ ክልል ደህንነት እና ፀጥታ ቢሮ ታማኝ የድርጅቱን የደህንነት አባላት በማሰማራት ሕዝባዊ ጥያቄውን  ሊያባብሱ ይችላሉ ያላቸውን የትግራይ ተወላጆች አፍኖ መውሰድ ጀምሯል።
የኦፕሬሽኑ ዋነኛ ትኩረት በትግራይ የሚገኙ የብልፅግና የአረና ፓርቲ አባላትና ደጋፊዎቻቸው መሆናቸውን ምንጮች አስረድተዋል።
የህወሓት ደህንነቶችና የፀጥታ ኃይሎች ትናንት ምሽት በመቀሌ የሚገኘው የአረና ፓርቲ ሊቀ መንበር አብርሃ ደስታን ከመንገድ ላይ አፍነው ለመውሰድ ያደረጉት ሙከራ አልተሳካም። ከእኩለ ሌሊት አንስቶ ይህ ዜና እስከተጠናከረበት ከቀኑ ዘጠኝ ሰዐት ድረስ የአብርሃ ደስታና የፓርቲው ሕዝብ ግንኙነት የአምዶም ገ/ስላሴ መኖሪያን እንደከበቡ ናቸው ተብሏል።
ወደ ሁለቱ ግለሰቦች መኖሪያ የሚገባና የሚወጣ ፣ እንዲሁም የቅርብ ግንኙነት አላቸው የተባሉ ሰዎች እየተያዙ ወደ ፖሊስ ጣቢያ መወሰዳቸውም ታውቋል።
ይህ በእንዲህ እንዳለ የትግራይ ሕዝብ አመጽ በእጅጉ ያስደነገጠው ህወሓት በኤርትራ የደምሂት አመራር የነበረው ፅጋቡ የተሰኘውን ወጣት ትናንት በአዲግራት ከተማ ውስጥ ከመንገድ ላይ አፍኖ እንደወሰደው ተጠቁሟል።

LEAVE A REPLY