ኢትዮጵያ ነገ ዜና፡– በአዲስ አበባ የሚኖሩ ዲፕሎማቶች ከውጪ ሀገር ሲመጡ “ከእንግዲህ በኋላ ለይቶ ማቆያ ወሸባ መግባት አያስፈልጋቸውም” ሲል የኢትዮጵያ መንግሥት አስታወቀ።
በኮሮና ቫይረስ ወረርሺኝ የተነሳ ከውጪ አገር የሚገቡ ሰዎች ለ14 ቀናት በአስገዳጅ ለይቶ ማቆያ እንዲገቡ የሚያስገድድ ህግ ቢኖርም የኢትዮጵያ መንግሥት ወረርሽኙ እንዲህ በተስፋፋበት ወቅት ህጉን በዲፕሎማቶች ላይ እንዳይተገበር ማዘዙ ግርምትን ፈጥሯል።
ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ዛሬ የወጣ ደብዳቤ እንደሚያሳየው ከሆነ ከዚህ በኋላ ከውጭ ሀገር የሚወጡ፣ ተቀማጭነታቸው በአዲስ አበባ የሆኑ የዲፕሎማቲክ ማኅበረሰብ አባላት መንግሥት ባዘጋጃቸው ለይቶ ማቆያ ሁቴሎች መግባት አያስፈልጋቸውም።
በመንግሥት ቀደም ሲል ማንኛውም ሰው ወደ ኢትዮጵያ ሲገባ በለይቶ ማቆያ እንዲያሳልፍ የሚያስገድደውን መመሪያ ዲፕሎማቶቹ በየኤምባሲዎቻቸው ወይም በመኖሪያ ቤታቸው ራሳቸውን ለይተው ማቆት እንደሚችሉ የተፈቀደላቸው መሆኑን ከመግለጫ አዘሉ ደብዳቤ መረዳት ችለናል፡፡
ይህ አዲስ መልዕክት የተላተፈላቸው ለሁሉም የዲፕሎማት ማኅበረሰብ አባሎች የተባበሩት መንግሥታት ድርጅቶችና የአፍሪካ ኅብረት ፓስፖርት ያላቸውና የቅርብ ቤተሰቦቻቸውን ያካተተ ነው፡፡