የህዳሴው ግድብ የሁሉም ኢትዮጵያዊያን አጀንዳ መሆኑን አቶ ገዱ አንዳርጋቸው አስታወቁ

የህዳሴው ግድብ የሁሉም ኢትዮጵያዊያን አጀንዳ መሆኑን አቶ ገዱ አንዳርጋቸው አስታወቁ

ኢትዮጵያ ነገ ዜና– ታላቁ የህዳሴ ግድብ የሁሉም ኢትዮጵያዊያን አጀንዳ መሆኑን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ገዱ አንዳርጋቸው ተናገሩ።

ዛሬ ለተፎካካሪ የፖለቲካ ፖርቲዎች የጋራ ምክር ቤት አባላት ግድቡን አስመልክቶ እየተከናወኑ ስለሚገኙ የዲፕሎማሲ ሥራዎች ገለጻ ባደረጉበት ወቅት ነው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ይህንን የተናገሩት።
ኢትዮጵያ የግድቡን ግንባታ ከመጀመሯ በፊት የዲፕሎማሲ ሥራውን መጀመሯን የጠቆሙት አቶ ገዱ አንዳርጋቸው፤ “የተፈጥሮ ሃብታችንን ፍትሃዊና ምክንያታዊ በሆነ መንገድ ለመጠቀም የማንንም ፍቃድ መጠየቅ አያስፈልገንም፤ ግድቡ ግንባታ ሌሎችን የመጉዳት ዓላማ እንደሌለው ለዓለምአቀፉ ማኅበረሰብ እያሳወቅን ነው” ሲሉ ተናግረዋል።

LEAVE A REPLY