ኢሕአዴግን ያፈረሱት ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ ለግንቦት 20 በዓል መልእክት አስተላለፉ

ኢሕአዴግን ያፈረሱት ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ ለግንቦት 20 በዓል መልእክት አስተላለፉ

Ethiopia's Prime Minister Abiy Ahmed (C) arrives at Khartoum international airport on June 7, 2019. - Ethiopia's prime minister arrived in Khartoum today seeking to broker talks between the ruling generals and protesters as heavily armed paramilitaries remained deployed in some squares of the Sudanese capital after a deadly crackdown, leaving residents in 'terror'. (Photo by ASHRAF SHAZLY / AFP) (Photo credit should read ASHRAF SHAZLY/AFP/Getty Images)

ኢትዮጵያ ነገ ዜና– “ኢሕአዴግ ፈራርሷል፣ ብልፅግና ተወልዷል” ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ህወሓት ለሚመፃደቅበት እና ነገ ለሚከበረው የግንቦት ሀያ በዓል የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል።

በትግራይ መቀሌ የመሸገው ህወሓት የአራት ድርጅቶች ጥምረት የሆነው ኢህአዴግ በቅርፅም በፖለቲካ ርዕዮት ዓለምም የተለየ መንገድ ይዞ “ብልፅግና” ወደ ተሰኘ ወጥ ፓርቲነት መቀየሩን ተከትሎ ከድርጅቱ በማፈንገጡ “ኢሕአዴግ” ነበር በሚል ያለፈ ድርጅት መጠሪያ መያዙ ይታወቃል።
ኢሕአዴግ ባይኖይኖርም፣ ቢፈራርስም ብልፅግና በመሪው አማካይነት ለግንቦት 20 እንኳን አደረሳችሁ ሲል ተከታዮን መልዕክት አስተላልፏል።
ግንቦት ሃያ የዘመናዊት ኢትዮጵያን ታሪክ ከቀየሩ ዕለታት መካከል አንዱ ነው፡፡ ኢትዮጵያን ዴሞክራሲያዊ፣ ፍትሐዊና ሰላማዊ ለማድረግ አያሌ ታጋዮች እጅግ ውድ የሆነውን የሰው ልጅ ነፍስ ሠውተዋል፡፡ የግንቦት ሃያ ታጋዮች የነፍስ ዋጋ የከፈሉለት ዓላማ ግፍና ጭቆና፣ አድሎና ወገንተኝነት ቆሞ፤ እኩልነት፣ ኅብረ ብሔራዊ አንድነት፣ ፍትሐዊ ተጠቃሚነትና የጋራ ብልጽግናን ለማረጋገጥ ነው፡፡
ግንቦት ሃያን ማክበር ያለብን እነዚህን ዓላማዎች እያሰብን መሆን አለበት፡፡ ቀኑን የምናስበው በግንቦት ሃያ ላይ ተቸክለን ሳይሆን ወደፊት እየሄድን የኋላውን እየገመገምን መሆን አለበት፡፡ ግንቦት ሃያን ያመጡ ታጋዮች ዓላማ ኢትዮጵያን ወደ ግንቦት ሃያ ሁለት መውሰድ እንጂ ወደ ግንቦት አሥራ ዘጠኝ መመለስ አልነበረም፡፡ ሀገራቸው በሁሉም መመዘኛ ግንቦት ሃያን አልፋ፣ ግንቦት ሃያ አንድንም ተሻግራ፣ ወደ ግንቦት 22 መድረስ ነበር፡፡
የግንቦት ሃያ ታጋዮችን ዓላማ የምናሳካው በሁለመናዋ ከግንቦት 19 የተሻለች ኢትዮጵያን መገንባት ከቻልን ብቻ ነው፡፡ የብልጽግና ጎዳናችን ዓላማ ግንቦት ሃያ ላይ ቆሞ ግንቦት አሥራ ዘጠኝን እያሰቡ መኩራራት ሳይሆን ሀገራችን ወደ ግንቦት 22 ማስፈንጠር ነው፡፡
ይህ ማለትም ሀገራችን ከነበረችበት አስከፊ ሁኔታ ማላቀቅ ብቻ ሳይሆን መድረስ ወደነበረባት የላቀ ደረጃ ማድረስ ነው፡፡ የግንቦት ሃያ የድል መታሰቢያ በዓልን ሰናከብር በተባበረ ክንድ ከግንቦት ሃያ የሚልቅ፣ ወደ ግንቦት 19 እንዳንመለስ የሚያደረግ ምጡቅ ሥርዓት ለመገንባት ቃላችን የምናድስበት እና ወደ ላቅ ውጤት ለመቀየር ወደ ተግባራዊ እንቅስቃሴ የምንገባበት መሆን ይገባዋል፡፡
ዘላለማዊ ክብርና ሞገስ በአጥንትና ደማቸው ኢትዮጵያና ሕዝቦቿን ላቆዩ ሰማዕታት

LEAVE A REPLY