በነጭ ፖሊስ ተረግጦ የሞተውን ጥቁር አሜሪካዊ ጉዳይ ኤፍ ቢ አይ መመርመር ጀመረ

በነጭ ፖሊስ ተረግጦ የሞተውን ጥቁር አሜሪካዊ ጉዳይ ኤፍ ቢ አይ መመርመር ጀመረ

ኢትዮጵያ ነገ ዜና– ሰሞኑን የቪዲዮ ምስሉ በማኅበራዊ ሚዲያዎች በመላው ዓለም በስፋት የተሰራጨውና በነጭ ፖሊስ አማካይነት በግፍ የተገደለው ጥቁር አሜሪካዊን ጉዳይ ኤፍ ቢ አይ ምርመራ መጀመሩን አስታወቀ።

አንድ ነጭ የፖሊስ ጥቁር አሜሪካዊውን በእግሩ ጉልበት አንገቱ ላይ ቆሞ ሲያሰቃየው ከቆየ በኋላ መተንፈስ አቅቶት ሲዝለፈለፍ፣ ተጠርጣሪው በበኩሉ “መተንፈስ አልቻልኩም፣ እባክህን አትግደለኝ” እያለ ሲማፀነው የሚያሳየው ምስል ከፍተኛ ተቃውሞዎችን እያስተናገደ ይገኛል።
ሟቹ የ40 ዓመት ጎልማሳ ጥቁር አሜረካዊ ጆርጅ ፍሎይድ ይባላል።
በፎርጂድ ምርት ተግባር ላይ የተሠማራ ነው የተባለው ሟቹ የ40 ዓመቱ ጎልማሳ ጥቁር አሜሪካዊ ጆርጅ ፍሎይድ፤ ጥቆማ የደረሰው  ፖሊስ በቁጥጥር ሥር ሊያውለው እንደመጣ ቢነገርም በቁጥጥር ሥር የዋለው ተጠርጣሪ ከህግ አግባብ ውጪ በአንድ ነጭ ፖሊስ አንገቱ ላይ ተረግጦ ሕይወቱን አጥቷል።
ሰኞ ዕለት የሞተው የአርባ ዓመቱ ጎልማሳ ማጅራቱን ከቆለፈው ፖሊስ ጋር ግብግብ አልባ የስቃይ ጊዜ ካሳለፈ በኋላ ወደ ሆስፒታል ተወስዶ ስለመሞቱ የሚኒሶታ ፖሊስም በይፋ እማኝነቱን ሰጥቷል።
“ድርጊቱ ሰቅጣጭና አሳፋሪ ነው” በማለት ነጩ ፖሊስ የሠራውን ከባድ ስህተት ያብጠለጠሉት፤ የሚኒሶታ ከንቲባ ጃኮብ ፍሬይ፤ በጋዜጣዊ መግለጫቸው ላይ “ያየሁት ነገር አስቀያሚ ነገር ነው፡፡ የተደረገው ነገር በየትኛውም መስፈርት ስህተት ነው። ጥቁር አሜሪካዊ መሆን የሞት ፍርድን ሊያሰጥ አይገባም” ሲሉም ተደምጠዋል።
በአሜሪካ ነጭ ፖሊሶች በጥቁሮች ላይ ተመጣጣኝ ያልሆነ እርምጃ መውሰዳቸው እየተለመደ መጥቷል። በቅርቡ  በሜሪላንድ አንድ የፖሊስ ባልደረባ ፓትሮል መኪና ውስጥ የነበረን ጥቁር አሜሪካዊ ተኩሶ መግደሉ የሚዘነጋ አይደለም።
በሚኒሶታ ሜኒያፖሊስ ያጋጠመውን አሳዛኝና አስደንጋጭ ክስተት ለ10 ደቂቃ ያህል የቀረጹ የአይን እማኞች፤ ፖሊሱ ጉልበቱን ከተጠርጣሪው አንገት እንዲያነሳ ሲጠይቁት፣
ሟችም መተንፈስ አልቻልኩም ከማለቱም በላይ እባክህን አትግደለኝ እያለ በተደጋጋሚ ሲማጸን እና አንድ የፖሊስ አባል ቀረጻ የሚያደርጉትን ሰዎች ሲከለክል ለዓለም ሕዝብ በግልጽ እንዲታይ አድርገዋል።

LEAVE A REPLY