የኢትዮጵያ የደህንነት ተቋም ቴክኖሎጂን ለማዘመን  እየሠራሁ ነው አለ

የኢትዮጵያ የደህንነት ተቋም ቴክኖሎጂን ለማዘመን  እየሠራሁ ነው አለ

ኢትዮጵያ ነገ ዜና–  የኢትዮጵያ ብቸኛው የደህንነት ተቋም የየኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት ኤጀንሲ የታዳጊዎችን የመረጃ ደህንነት አቅም ለማሻሻል ይረዳል የተባለ ስምምነት መፈረሙ ተሰማ

ፓወር ከተሰኘ በሳይንስ፣ በቴክኖሎጂ፣ በኢንጅነሪንግ እንዲሁም በሒሳብ ዘርፎች ከሚሠራ ድርጅት ጋር  ስምምነቱ የተፈረመ መሆኑን ኤጀንሲው በድኅረ ገፁ ይፋ አድርጓል፡፡
ስምምነቱ በሳይበር ደህንነት ዙሪያ የፈጠራ አቅም ያላቸው ታዳጊዎችን አቅም የሚያሻሽል እንደሆነም ተነግሮለታል።
ስምምነት ከ3 እስከ 5 ዓመት እንደሚቆይም ታውቋል፡፡
 በቅርቡ የሳይበር ተሰጥዖ ውድድር እንደሚያዘጋጅ የጠቆመው ኤጀንሲው  በዘርፉ ጥሩ የፈጠራ አቅም ያላቸው ወጣቶች እንዲሳተፉና በዕድሉ ተጠቃሚ እንዲሆኑ ጋብዟል።

LEAVE A REPLY