ዶናልድ ትራምፕ ለማኅበራዊ ሚዲያዎች የተሰጠውን ሕጋዊ ከለላ የሚያነሳ ፊርማ አኖሩ

ዶናልድ ትራምፕ ለማኅበራዊ ሚዲያዎች የተሰጠውን ሕጋዊ ከለላ የሚያነሳ ፊርማ አኖሩ

ኢትዮጵያ ነገ ዜና– የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ለማኅበራዊ ሚዲያዎች የተሰጠውን ሕጋዊ ከለላ የሚያነሳ ፊርማቸውን ማኖራቸው ተሰማ።

የፕሬዝዳንቱ ፊርማ ተቆጣጣሪዎች ፌስ ቡክና ትዊተር ላይ ክትትል በማድረግ ሕጋዊ ርምጃ እንዲወስዱ እድል በከፍተኛ ሁኔታ እንደሚሰጣቸው ተነግሯል።
ዶናልድ ትራምፕ ፊርማቸውን ባኖሩበት ወቅት “ማኅበራዊ ሚዲያዎች ቁጥጥር የማይደረግበት አቅም ነበራቸው” ሲሉ ቢወነጅሉትም ይህ የፕሬዝዳንቱ ውሳኔ ግን ሕጋዊ ተግዳሮቶች ይገጥሙታል እየተባለ ነው።
የሕግ ባለሙያዎች የሕግ መወሰኛው ምክር ቤት ወይም የፍትህ አካሉ እነዚህ ተቋማት ያላቸውን የህግ ከለላ ለማንሳት ሊሳተፉ እንደሚገባ ጠቁመው፤ ትራምፕ የማኅበራዊ ሚዲያዎችን የወግ አጥባቂዎችን ድምጽ በተደጋጋሚ ያፍናሉ ሲሉ ወቅሰዋል።
ዶናልድ ትራምፕ ከትናንት በስቲያ በቲውተር ሰሌዳ ላይ ከተጻፈው ሐሳብ ሥር “የትራምፕ መልዕክት እውነታነት ሊጤን ይገባዋል” የሚል ምልክት ቲውተር ማድረጉን ተከትሎ ፕሬዝዳንቱ ምርጫ ላይ ጣልቃ ይገባል ሲሉ ማኅበራዊ ሚዲያውን ወንጅለውታል።
ቲውተር መልዕክቶቹ ዳግም ሊፈተሹ እንደሚገባ የሚገልጽ መልዕክት የሚያስቀምጥባቸው ተጠቃሚ የሐሰት ወይም ያልተረጋገጠ ሐሳብ ሲጽፍ መሆኑን በመግለፅ የፕሬዝዳንቱን ሐሳብ እውነታነት እንደሚጠራጠረው ዳግም አረጋግጠጧል።

LEAVE A REPLY