የድንበር ተሻጋሪ የጭነት ተሽከርካሪዎች ተርሚናል ደዋሌ ላይ ሊገነባ ነው

የድንበር ተሻጋሪ የጭነት ተሽከርካሪዎች ተርሚናል ደዋሌ ላይ ሊገነባ ነው

ኢትዮጵያ ነገ ዜና– የፌደራል ትራንስፖርት ባለሥልጣን ለድንበር ተሻጋሪ አሽከርካሪዎች መሰረታዊ የሚባሉ አገልግሎቶችን ማቅረብ የሚቻልበት ተርሚናል “ደወሌ” መግቢያ ላይ ለመገንባት ከሶማሌ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ቦታ ተረክቢያለሁ አለ፡፡

ተርሚናሉ በፍጥነት ተገንብቶ አሽከርካሪዎች ሊያገኟቸው የሚገባቸውን መሰረታዊ አገልግሎቶች ለማቅርብ እንደሚያስችል ተጠቁሟል። የሚገነባው ተርሚናል አሽከርካሪዎች ጭነት ለመጫን ጅቢቲ ከመግባታቸው በፊት በተርሚናሉ የጭነት ተራቸውን የሚጠብቁ ሲሆን፣ ለዚህ የሚረዳ የመታጠቢያ፣ የማረፊያ፣ የምግብ፣ የጤና ምርመራና ሕክምና ፤ እንዲሁም ሌሎች መሰረታዊ የሚባሉ አገልግሎቶችን ማቅረብ የሚያስችል እንደሆነ ተናግሯል።
ተርሚናሉ የድንበር ተሻጋሪ የጭነት አሽከርካሪዎች ጅቡቲ ወደብ ከገቡ በኋላ የጭነት ተራ እስኪደርሳቸው በመጠበቅ ቀናትን የሚያሳልፉበት ወቅት የሚያወጡትን ወጪ፣ የሚያጋጥማቸውን መጉላላት ጭምር ይቀንሳል ተብሏል።

LEAVE A REPLY