ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ኮሮና ሳያጠፋን እናጥፋው አሉ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ኮሮና ሳያጠፋን እናጥፋው አሉ

ኢትዮጵያ ነገ ዜና– ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ የኮሮና ቫይረስ ሳያጠፋን እናጥፋው ሲሉ የኢትዮጵያ ሕዝብ ከመቼውም ጊዜ በላይ ጥንቃቄ እንዲያደርግ አሳሰቡ።

“የኮሮና ወዳጅ ማን እንደሆነ ደርሰንበታል፣ መዘናጋት ይባላል፡፡ ኮሮና ከመዘናጋት ጋር ከተባበረ አንችለውም፤ ሁለቱን መነጣጠል አለብን፤ ሰሞኑን በኮሮና የሚያዙ ሰዎች ቁጥር እየጨመረ የመሄዱ ምክንያት ኮሮናና መዘናጋት ግንባር በመፍጠራቸው ነው” ሲሉ በማኅበራዊ ሚዲያ መልዕክት ያስተላለፉት ዶክተር ዐቢይ አሕመድ፤ የኢትዮጵያ ሕዝብ ከሰሞነኛ መዘነጋቱ እንዲጠነቀቅ ምክር ለግሰዋል።
“ኮሮና ማንን እንደሚጠላና እንደሚፈራ ዐውቀነዋል፤  ኮሮና ጥንቃቄ የሚባለውን ፈጽሞ አይወደውም፣ ጥንቃቄ ባለበት ወይ አይደርስም፤ ወይ የከፋ ጉዳት አያደርስም። እንደምታዩት ሁለት፣ ሦስት፣ ዐሥር፣ ሠላሳ፣ ሰባ፣ እያለ መቶ ገብቷል። ሁኔታው የሚያሳየው ኮሮና እያመረረ፣ እኛ እየተዘናጋን መምጣታችንን ነው።
ኮሮና ተዘናግቶ እኛ ብንኖር ነበር ጥሩ። ወይ ተባብረን እንነሣበት፤ አልያም ኮሮናና መዘናጋት ተባብረው ይደቁሱን?
ምርጫው ከሁለቱ አንዱ ነው ሁኔታው ሳይመርብን፣ እኛ እናምርበት፣ ኮሮና ሳያሸንፈን እናሸንፈው። ኮሮናን የማሸነፊያ ቀን ዛሬ፣ የማሸነፊያ ሰዐት አሁን ነው፤ የሚያሸንፈውም ሰው እርስዎ ነዎት” ሲሉ  መልዕክት አስተላልፈዋል።

LEAVE A REPLY