በኢትዮጵያ ተጨማሪ 137 ሰዎች በኮሮና ተያዙ፣ ሰምንተኛ ሞትም ተመዝግቧል

በኢትዮጵያ ተጨማሪ 137 ሰዎች በኮሮና ተያዙ፣ ሰምንተኛ ሞትም ተመዝግቧል

ኢትዮጵያ ነገ ዜና– በኢትዮጵያ ባለፉት 24 ሰዐታት ውስጥ በተደረገው 5.015 ሰዎች የላብራቶሪ ምርመራ 137 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ እንደተገኘባቸው የጤና ሚኒስቴር ገለፀ።

በዚህም አጠቃላይ በሀገሪቱ ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር 968 ደርሷል ያለው የጤና ሚኒስቴር፤ በተጓዳኝ ሕመም ምክንያት ሕክምና ላይ የነበሩ የ62 ዓመት ዕድሜ ያላቸው ወንድ አዛውንት መሞታቸውን ተከትሎ በበሽታው ሕይወታቸውን ያጡ ሰዎች ስምንት መድረሳቸውን ይፋ አድርጓል።
አዛውንቱ ለኮሮና ቫይረስ በሽታ በተደረገ ምርመራ ናሙና ከተወሰደ በኋላ የምርመራ ውጤቱ ሳይደርስ ሕይወታቸው ቢያልፍም፤ በምርምራው ውጤቱ የኮቪድ 19 ቫይረስ ተገኝቶባቸዋል።

LEAVE A REPLY