የኢሳያስ አፈወርቂ ሁለተኛ ሰው የነበረው ጴጥሮስ ሰለሞን “ህዝባዊ ግንባር (ሻቢያ) አሥመራ ስንገባ እና ወያኔ አዲስ አበባ ሲገቡ፣ እኛ ምፅዋ ወደብ እንደያዝን፣ እነሱ ደግሞ አሰብን ለኢትዮጵያ ያስቀራሉ የሚል ግምት ነበረን። መለስ ዜናዊ ተነስቶ ደጋግሞ ‘ኢትዮጵያ ወደብ ኑሯት አያውቅም’ ብሎ ሁለቱን ወደቦች ሲያስረክቡን፣ እኔ በግሌ ክው ነበር ያልኩት። የኢትዮጵያ ህዝብ ገደሉት ነበር ያልኩት!”
ይህን የተናገረው አቶ ጴጥሮስ ሰለሞን ኢሳያስ አፈወርቂ ከ G-15 ጋር አስሮት ዛሬ በህይወት ይኑር አይኑር አይታወቅም። ይህን ታሪካዊ ምስክርነት ሲስጥ ግን አንድ ታዋቂ ኢትዮጵያዊ ፓይለት አብሮት ነበር። (እኚህ ኢትዮጵያዊ ፓይለት በቅርቡ አግኝተን ምስክርነታቸውን ለኢትዮጵያ ህዝብ እንዲሰጡ እንጋብዛቸዋለን።)
ምንም እንኳን የኢህአዴግ ጦር ቀድሞ አሰብ ወደብን ቢይዝም፣ ኗሪው ህዝብ ከ90% በላይ አማርኛ ተናጋሪ መሆኑ ለመለስ የጎን ውጋት ነበር። ለዚህም መፍትሄ ብሎ ያወጣው እቅድ “አሰብን ተሎ ለቃችሁ ካልወጣችሁ ሻቢያ ያጠፋቹሃል” የሚል አሸባሪ ወሬ ለቆ ህዝቡ ጨርቄ ማቄ ሳይል ከአሰብ ተንጋግቶ እንደጎርፍ መውጣት ጀመረ።
ለዚሁ ፕሮጀክት ይሳካ ዘንድ እነ መለስም ግዙፍ የኢት. የንግድ መርከቦች ወደ አሰብ እያስጠጉ ጢም ብለው እስኪሞሉ ድረስ አስብን የማራቆት ዘመቻ አጧጧፉ! አሰብን ከኢትዮጵይውያን የማፅዳት ዘመቻው ቀጠለ።
መርከቦቹም የቻሉትን እየጫኑ ወደ ጅቡቲ መሰመር እየወሰዱ ህዝቡን አራገፉት። ከሞት የተረፉት የአሰብ ተፈናቃዮች በአዲስ አበባ አራዳ ጊዮርጊስ ቅጥር ግቢ፣ በጃን ሜዳ እና በሌሎች የጎዳና ተዳዳሪ ሆነው እንባቸውን እየዘሩ ተበታትነው እንደወጡ ቀሩ። ህፃናት የታቀፉ እናቶች እንባቸውን እየዘሩ ለነ ስዬ አብርሃ አቤት ቢሉ “ኤርትራ ውስጥ የነበራችሁት የደርግ ሰላዮች ሁናችሁ ነው እንጂ በሌላ አይደለም” እያለ በሀዘናቸውና መከራቸው ላይ እሳት ለቀቀበት። ግንቦት 20 ባንዳዎች የትግራይ ተወላጆችን ከፊት ለፊት አሰልፈው ኢትዮጵያን ማዋረድና እና በዘር ማናከስ የጀመሩበት የጠላት ቀን ነው። ይህ ቀን በኢትዮጵያውያን ድል አድርጊነት ይተካል!