ኢትዮጵያ ነገ ዜና፡– በጽኑ ሕሙማን ሕክምና ክፍል ይገኙ ከነበሩት ታማሚዎች መካከል ሦስቱ ሰዎች መምታቸውን ተከትሎ በአጠቃላይ በኢትዮጵያ በበሽታው የምቱ ሰዎች ቁጥር 11 ደርሷል።
ከዚሁ ጎን ለጎን በኢትዮጵያያ ባለፉት 24 ሰዐታት በተደረገ የላብራቶሪ ምርመራ ተጨማሪ 109 ሰዎች ላይ የኮሮና ቫይረስ እንደተገኘባቸው የጤና ሚኒስቴር ገልጿል። በአጠቃላይ በሀገሪቱ በኮሮና ቫይረስ የተያዙ ሰዎች ቁጥርም 1.172 (አንድ ሺኅ አንድ መቶ ሠባ ሁለት) ደርሷል።
ባለፉት 24 ሰዐታት ዉስጥ ለ 2 ሺኅ 836 ሰዎች ምርመራ ተደርጓል።
ቫይረሱ ከተገኘባቸው 109 ሰዎች መሀል 61ዱ ወንዶች ሲሆኑ 48 ቱ ደግሞ ሴቶች እንደሆኑና፤ እድሜያቸዉም ከ5 እስከ 70 ዓመት የሚደርስ መሆኑ ተነግሯል።
99ኙ የቫይረሱ ተጠቂዎች ከአዲስ አበባ፣ 5 ሰዎች ከኦሮሚያ ክልል፣ 2 ሰዎች ከትግራይ ክልል፣3 ሰዎች ከሀረር ክልል ሲሆን፤ 2 ሰዎች የውጭ ሀገራት የጉዞ ታሪክ ያላቸው፣ 13 ሰዎች በበሽታው ከተያዘ ሰው ጋር ግንኙነት ያላቸው፣ ቀሪዎቹ 94 ሰዎች የውጭ ሀገር የጉዞ ታሪክና በበሽታው ከተያዘ ሰው ጋር ግንኙነት የሌላቸዉ መሆኑን የጤና ሚኒስቴር መግለጫ ያሳያል።
በትናንትናው ዕለት 11 ሰዎች (2 ከትግራይ፣9 ከአፋር ክልሎች) ከበሾታው አገግመዋል ያለው ሚኒስቴሩ አጠቃላይ ያገገሙ ግለሰቦች ቁጥር 209 ቢደርስም
አሁንም በጽኑ ህሙማን ማከምያ ዉስጥ አራት ታማሚዎች እንደሚገኙ ጠቁሟል።