ኢትዮጵያ ነገ ዜና፡– የታገቱት የአማራ ክልል ተወላጅ የሆኑ የዮንቨርስቲ ተማሪዎች ከታገቱ ዛሬ ስድስት ወር ሞልቷቸዋል። እስከሁን ምንም አይነት መረጃ አልተገኘም።
ከሚማሩበት ምዕራብ ኦሮሚያ ከሚገኘው ደምቢዶሎ ዮንቨርስቲ ወደ መኖሪያ ቀያቸው በማምራት ላይ የነበሩት ተማሪዎች ማንነታቸው ባልታወቁ ሰዎች ከታገቱ በኋላ ወላጆቻቸው ልጆቻቸው ችግር ላይ እንደወደቁ የሰሙት ህዳር 24 ቀን 2012 ዓ.ም ሲሆን፤ ራሳቸው ተማሪዎቹ በአጋቾቹ ትዕዛዝ ስልክ እንዲደውሉ ከተደረገ በኋላ ነበር።
ይሁን እንጂ መጀመሪያ ላይ የታገቱትን ተማሪዎች አስለቅቀናል በማለት ሀሰተኛ መረጃ ሰጥቶ የነበረው መንግሥት በቀናት እድሜ ውስጥ የልጆቹን አለመለቀቅ አምኖ በፍጥነት ተማሪዎቹን ከወላጆቻቸው እቀላቅላለሁ ቢልም ምንም ነገር ሳይሰማ ስድስት ወራት ተቆጥረዋል።
ይሄን ተከትሎ ዛሬ ኢትዮጵያውያን በማኅበራዊ ሚዲያዎች አማካይነት የታገቱ ሴት ተማሪዎች ፎቶዎችን በማኅበራዊ ሚዲያዎችና በተለያዮ መገናኛ ብዙኃን ድኅረ ገፆች ላይ በስፋት ሲያሰራጬ ታይታዋል።