85 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ተገኘባቸው ፤ 12ኛ ሞትም ዛሬ ተመዝግቧል

85 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ተገኘባቸው ፤ 12ኛ ሞትም ዛሬ ተመዝግቧል

ኢትዮጵያ ነገ ዜና– በኢትዮጵያ ባለፉት 24 ሰዐታት ውስጥ ለ2 ሺኅ 926 ሰዎች በተደረገ  የላብራቶሪ ምርመራ 85 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ እንደተገኘባቸው የጤና ሚኒስቴር ገለፀ።

ይህን ተከትሎ አጠቃላይ በሀገሪቱ ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው ሰዎች 1ሺኅ 257 ደርሷል።
ዛሬ ቫይረሱ እንደተገኘባቸው የተረጋገጡ ሰዎች ከ1 ወር እስከ 65 ዓመት የእድሜ ክልል ውስጥ የሚገኙ ሲሆን፣ በፆታ ረገድ 51 ወንድና 34 ሴቶች ኢትዮጵያውያን እንደሆኑም ታውቋል።
ቫይረሱ የተገኘባቸው ሰዎች 72 ሰዎች ከአዲስ አበባ ሲሆኑ፣ 4 ሰዎች ከትግራይ ክልል፤ 5 ኦሮሚያ ክልል፣ 1 ሰው ከአማራ ክልልና 3 ሰዎች ከሶማሌ ክልል እንደሆነ መግለጫው ያሳያል።
በዚህም መሰረት ዛሬ ቫይረሱ ከተገኘባቸው 85 ሰዎች መሀል፤ 19 ሰዎች የውጭ ሀገር ጉዞ ታሪክ ያላቸው፣ 18 ሰዎች በበሽታው ከተያዘ ሰው ጋር የታወቀ ግንኙነት ያላቸው እንዲሁም 48 ሰዎች ደግሞ የውጭ ሀገር ጉዞ ታሪክም ሆነ በበሽታው ከተያዘ ሰው ጋር የታወቀ ግንኙነት የሌላቸው መሆናቸው ተነግሯል።
በሌላ በኩል በትላንትናው ዕለት 8 ሰዎች (3 ከኦሮሚያ ክልል፣ 5 ከአዲስ አበባ) ያገገሙ ሲሆን፣ በሀገሪቱ ከበሽታው ያገገሙ ሰዎች ቁጥር 217 ደርሰዋል ያለው የጤና ሚኒስቴር፤ አሁን ላይ በኢትዮጵያ ቫይረሱ ተገኝቶባቸው በለይቶ ህክምና ውስጥ 1 ሺኅ26 ሰዎች የሚገኙ ሲሆን፣ አራት ሰዎች በጽኑ ህክምና ክፍል ክትትል እየተደረገላቸው እንደሚገኙ ይፋ አድርጎል።
ይህ በእንዲህ እንዳለ የኮሮና ቫይረስ በምርመራ ተገኝቶበት በየካ ኮተቤ ሕክምና ሲደርግለት የነበረ፣  (ቀደም ሲል ተጓዳኝ ሕመም ያለበት) እና በፅኑ ሕክምና ላይ የነበረ የ30 ዓመት ኢትዮጵያዊ በትላንትናው ዕለት ሕይወቱ እንዳለፈ ሚኒስቴሩ ባወጣው ዕለታዊ መግለጫ ላይ አስታውቋል።
በዚህም አጠቃላይ በኢትዮጵያ ቫይረሱ የተገኘባቸው እና ሕይወታቸው ያለፈ ሰዎች ቁጥር ዐሥራ ሁለት  ደርሷል፡፡

LEAVE A REPLY