ኢትዮጵያ ነገ ዜና፡– “ቡድን 7” የተሰኘው የዓለማችን ኃያላን አገሮች ስብሰባ ጉዳይ ማወዛገብ እንደጀመረ በመነገር ላይ ነው።
ቀደም ሲል የአገራቱን ስብሰባ በሰኔ ወር ለማካሄድ ታቅዶ የነበረ ቢሆንም፤ የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ስብሰባው ቢያንስ እስከ መጪው መስከረም ወር እንዲራዘም ሰሞኑን ጥያቄ አቅርበዋል ነው የተባለው።
ትራምፕ ሩሲያ ዳግም ቡድኑን እንድትቀላቀል መፈለጋቸው ለስብሰባው መራዘም ምክንያት እንደሆነ የሚጠቁሙት መረጃዎች፤ ካናዳ እና ብሪታንያ በአንጻሩ የሩሲያ ዳግም ቡድኑን መቀላቀሏን በጥብቅ እንደሚቃወሙ ያሳያል።
የሩሲያ ቀደም ሲል ቡድን 8 ከተሰኘው የሃያላን አገሮች ስብስብ የተባረረችው፣ ከ6 ዓመታት በፊት በዩክሬን ስር ስትተዳደር የነበረችውን የክሬሚያን ልሳነ ምድር ወደ ራሷ ከቀላቀለች በኋላ መሆኑ ይታወቃል።
” ቡድን 7 ጊዜ ያለፈበት ስብስብ በመሆኑ፣ ሩሲያን ጨምሮ ሌሎችንም ማካተት ይኖርበታል” እያሉ በመሞገት ላይ ቢሆኑም ብሪታኒያ፣ ፈረንሳይ፣ ጀርመን፣ አሜሪካ፣ ጃፓን፣ ጣልያንና ካናዳን የያዘው የሠባቱ ሀገራት ጉባዔ በቅርቡ ይካሄዳል ተብሏል።