ኢትዮጵያ በድኅረ ኮረና ለጉብኝት ከሚመረጡ 7 የዓለም   ሀገራት አንዷ እንደምትሆን ፎርብስ መጽሔት...

ኢትዮጵያ በድኅረ ኮረና ለጉብኝት ከሚመረጡ 7 የዓለም   ሀገራት አንዷ እንደምትሆን ፎርብስ መጽሔት ገለፀ

ኢትዮጵያ ነገ ዜና– ኢትዮጵያ በድኅረ ኮሮና ዘመን (የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ መጥፋት) በኋላ በጎብኚዎች ከሚመረጡ ሠባት የዓለም ሀገራት መካከል አንዷ እንደምትሆን ፎርብስ መጽሔት ከወዲሁ ግምቱን አስቀምጧል።

አሁን ላይ ዓለምን እያስጨነቀ ከሚገኘው ከኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ መጥፋት በኋላ፤ ኢትዮጵያን ጨምሮ ሠባት ሀገራት ተመራጭ የቱሪዝም መዳረሻ እንደሚሆኑ እና በብዙ ሀገር ዜጎች እንደሚገኙ ጠቁሟል፤ ፎርብስ።
ኢትዮጵያ ባላት የተፈጥሮ ሃብት፣ ባህል እና ታሪክ፣ ቀዳሚዋ የጎብኚዎች መዳረሻ እንደምትሆን የተነበየው ፎርብስ መጽሔት፤  ኢትዮጵያ ቀደምት የሰው ዘር መገኛ፣ ቀደምት ሥልጣኔ እና ቅኝ ገዢዎችን በጦርነት ያሸነፈች ብቸኛዋ አፍሪካዊት ናት ሲልም በዘገባው ገልጿል።
የተለያዩ ውብ ተፈጥሯዊ እይታዎች የታደለች ሀገር መሆኗን ፣ የኢትዮጵያውያን ባህል ብቻ የሆነውን እንጀራን በእጅ የመብላት ልምድም ሁሉም በሕይወቱ አንድ ጊዜ ሊሞክረው የሚገባ መሆኑም ተነግሯል።
ከኢትዮጵያ በተጨማሪ ኢራን፣ ማይናማር፣ ጆርጂያ፣ ፊሊፒንስ፣ ስሎቬኒያ እና አፍሪካዊቷ ቱኒዚያ በኮሮና ማግስት ወይም ድኅረ ኮሮና ዘመን የጎብኚዎች መዳረሻ ይሆናሉ ተብለው በፎርብስ መጽሔት ተለይተዋል።

LEAVE A REPLY