ከለይቶ ማቆያ ያመለጡት 5ቱ የሲዳማ ነዋሪዎችን ተከትሎ 411 ሰዎች በፀጥታ ኃይሎች ተያዙ

ከለይቶ ማቆያ ያመለጡት 5ቱ የሲዳማ ነዋሪዎችን ተከትሎ 411 ሰዎች በፀጥታ ኃይሎች ተያዙ

ኢትዮጵያ ነገ ዜና– ትናንትና ከተገለፀውና ከቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ለይቶ ማቆያ አምልጦ ከጠፋው በኮሮና ቫይረስ ከተያዘ ወጣት በተጨማሪ ሌሎች አምስት ሰዎች ከአዲስ አበባ ገና ውጤታቸው ሳይገለፅ ወደ ሲዳማ ዞን መግባታቸውን የደቡብ ክልል ጤና ቢሮ ገለፀ።

እነዚህ 5 ግለሰቦች ትላንት በኮሮና ቫይረስ (ኮቪድ-19) መያዛቸው ከተረጋገጠ 95 ሰዎች መካከል የተካተቱ መሆናቸውም ተነግሯል።
በቫይረሱ ተጠርጥረው ውጤት በመጠባበቅ ላይ እያሉ ካመለጡትና (በኋላ በቫይረሱ መያዛቸው የተረጋገጠ) እስካሁን  ከአምስቱ ግለሰቦች መካከል ሦስቱ  በደህንነት አባላት፣ በደቡብ ክልል የፀጥታ ኃይሎችና ፌደራል ፖሊስ አባላት ክትትል በቁጥጥር ሥር ውለዋል።
በኮቪድ 19 ቫይረስ ተይዘው ካመለጡት የሲዳማ ዞን ነዋሪዎች መሀል፤ ሁለቱ ወደመኖሪያ አካባቢያቸው ሲያዙ፣ አንደኛው ሰው ደግሞ “ጥቁር ወሃ ” የተሰኘች አነስተኛ ከተማ ላይ መያዙን የሚያሳየው መግለጫ፤ በአሁን ሰዐት ሁለቱ ግለሰቦች  ይርጋለም ማከሚያ ማዕከል ውስጥ እንደሚገኙ፣ አንደኛው ታማሚ ሀዋሳ ማከሚያ ማዕከል ውስጥ ሕክምና በመከታተል ላይ መሆኑን አስታውቋል።
ከእነዚህ ግለሰቦቹ ጋር ንክኪ ያላቸው የተለያዩ ሰዎች መያዛቸውን የጠቆመው የደቡብ ክልል መግለጫ፤ “በንሳ” ወረዳ ላይ 141 ሰዎች፣ ይርጋለም ከተማ ላይ 180 ሰዎች፣ ሀዋሳ ከተማ ላይ 90 ሰዎች፤ በአጠቃላይ 411 ሰዎች በደህንነት እና የፀጥታ አባላቱ ፈጣን ክትትል መያዛቸውን አረጋግጧል።
ከአምስቱ አምላጮች መሀል ያልተገኙት ሁለቱን ሰዎች እስካሁን በፀጥታ መዋቅሩ እየተፈለጉ ነው። አንደኛው ግለሰብ ሽፋ ወረዳ የሚኖር ዕድሜው 18 የሆነ፣ ሁለተኛው በንሳ ዳዬ የሚባል ዕድሜው 23 ዓመት የሚገመት ወጣት  መሆኑን መረጃዎች ያሳያሉ።

LEAVE A REPLY