ኢትዮጵያ ነገ ዜና፡– የአዲስ አበባ ውሃና ፍሳሽ ባለሥልጣን ለሁለት ዓመታት በከተማዋ የሚገኙ ትላልቅ የመንግሥት ተቋማትን ጨምሮ ግዙፍ ድርጅቶች ክፍያ አልፈጸሙልኝም አለ።
ባለሥልጣን መሥሪያ ቤቱ ዛሬ ይፋ እንዳደረገው ከፍተኛ በጀት ያላቸው ከ3 ሺኅ 5 መቶ በላይ የሚሆኑ ታላላቅ ድርጅቶች የውሃ አገሌግሎት ሳይከፍሉ ከቆዮ ሁለት ዓመት ሆኗቸዋል።
የከተማ መስተዳደሩ ዉሃና ፍሳሽ ባለሥልጣን፤ ውዝፍ ዕዳ ያለባቸው እነዚህ የተለያዮ ተቋማት በቀጣዮቹ ሁለት ወራት ውስጥ ክፍያቸውን የማያጠናቅቁ ከሆነ አገልግሎቱን የማቋረጥ እርምጃ ለመውሰድ እንደሚገደድም ገልጿል።