ጠቅላይ ዐቃቤ ህግ ለአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን የ20 ሚሊየን ብር የገንዘብ ድጋፍ...

ጠቅላይ ዐቃቤ ህግ ለአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን የ20 ሚሊየን ብር የገንዘብ ድጋፍ አደረገ

ኢትዮጵያ ነገ ዜና– ጠቅላይ ዐቃቤ ህግ የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን የተጠርጣሪ ማቆያዎችን ለማሻሻል እንዲያውለው የ20 ሚሊየን ብር የገንዘብ ድጋፍ አደረገ፡፡

የድጋፍ ስምምነቱን ጠቅላይ ዐቃቤ ህጓ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ ከአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ጌቱ አርጋው ጋር ዛሬ ሲፈራረሙ ታይቷል።
የእስረኛ ማቆያዎች አካባቢ የሚስተዋሉ ችግሮችን ለመቅረፍ ድጋፉ ከፍተኛ አስተዋጽኦ ይጫወታል ያሉት አዳነች አቤቤ፤ ገንዘቡ በተለያዩ አካባቢዎች 10 የእስረኛ ማቆያ ጣቢያዎችን ለመገንባት እና በምርመራ ሂደት ውስጥ ለሚያስፈልጉ የቴክኖሎጂ ግብዓቶች ማሟያ እንደሚውል አስታውቀዋል።
ባለፉት ሁለት ዓመታት ማረሚያ ቤቶች እና ፖሊስ ጣቢያዎች ላይ የሚደርሰውን የሰብኣዊ መብት ጥሰት ለማሻሻል፣ እንዲሁም እንዳይደገም ለማድረግ ትላልቅ ውሳኔዎች መወሰናቸውን፤ እንዲሁም ከ100 ሺኅ በላይ እስረኞችም እንዲለቀቁ መደረጋቸውን ጠቅላይ ዐቃቤ ህጓ ጠቁመዋል።
 ፖሊስ ጣቢያዎች ተጠርጣሪዎችን የሚይዙበት መንገድ የተሻለ እንዲሆን ተቋማቸው ድጋፉን አጠናክሮ  እንደሚቀጥል ያስታወቁት አዳነች አቤቤ፤ የአዲስ አበባ ፖሊስ የተደረገለትን ድጋፍ በ6 ወራት ውስጥ እንዲተገብር መመሪያ ተቀምጦለታል።

LEAVE A REPLY